Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያስብ ፡ ኖሮ ኃጢአቴን ፡ ልናዘዝ ፡ ህሊናዬ ፡ ሲወቅሰኝ ምህረትም ፡ ልማጠነው ፡ ደጅ፡ ባስጠናኝ ውድቀቴ ፡ ሳይገደው ፡ ባላገጠ ፡ ፊቱ ፡ በጠቆረ ፍቅሩ ፡ ቀዝቅዞብኝ ፡ ድምጹ ፡ በሻከረ እንኳንስ ፡ ልጁ ፡ ሊያረገኝ ሥሙን ፡ ለመጥራት ፡ ባስከፈለኝ (፪x) እንኳንስ ፡ ቤቱ ፡ ለመኖር ከደጁ ፡ መጣል ፡ በተሳነኝ ከደጁ ፡ መጣል ፡ በናፈቀኝ አዝ፦ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም ከቶ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ወሰን ፡ ቁጥር ፡ የለው ከወዳጅም ፡ ወዳጅ ፡ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ የወደቀን ፡ አይቶ ፡ እንዳላየ ፡ አይሸሽ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም (፬x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያይ ፡ ኖሮ እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያስብ ፡ ኖሮ ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ሳጣ ፡ ሲጐድል ፡ ሙሉ ፡ ቤቴ ከንፈር ፡ ቢመጥልኝ ፡ ርቆ ፡ ከአጠገቤ ባሕሪው ፡ ተለውጦ ፡ ቀስ ፡ እአለ ፡ በሽሽ ፡ በራቀ ወዳጅነት ፡ ቀርቶ ፡ አዛኝ ፡ በመሰለ ነፍሴን ፡ ሲከፋት ፡ ዝም ፡ ስል ሃዘኔ ፡ ንቀት ፡ ቢመስል (፪x) ውስጤ ፡ ማቅ ፡ ለብሶ ፡ ከሰው ፡ ቢያርቅ እንደኮራሁ ፡ ቢያስበኝ ፡ እንደተኩራራሁ ፡ ቢያስበኝ አዝ፦ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም ከቶ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ወሰን ፡ ቁጥር ፡ የለው ከወዳጅም ፡ ወዳጅ ፡ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ የወደቀን ፡ አይቶ ፡ እንዳላየ ፡ አይሸሽ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም (፬x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም