Loading
Singer
ፈውሴ ለነፍሴ በመመለሴ እንደሆነ አውቄያለሁ - መልሰኝ እመለሳለሁ መልሰኝ መልሰኝ መልሰኝ እመለሳለሁ ፈውሰኝ ፈውሰኝ ፈውሰኝ ድኜ ቀራለሁ እርኩሰት አብዝተን በደል ጨምረናል አመጽን በመዝሙር በጩኸት ከድነናል - ማረን ይቅር በለን ተመለሱ የሚል ምክርህን ንቀናል ልዑሉ በሰማይ መኖርህን ረስተናል - ማረን ይቅር በለን አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን አቤቱ ፈውሰን እንፈወሳለን አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን አቤቱ መልሰን እንመለሰላን ኦ ማረን - ማረን ይቅር በለን /4/ ጥላቻና ትዕቢት ንቀት አስክሮናል ይቅር ማለት ከብዶን ከምህረት ጎድለና - ማረን ይቅር በለን ፍሬ ሳናፈራ እንባ ማብዛታችን ከቶ አልጠቀመንም ግብዝነታችን - ማረን ይቅር በለን ጎራ እየለየን ውጊያ ሰልጥነናል ክቡር ደምህን ረግጠን ወንድምን ገድለናል - ማረን ይቅር በለን የሰጠኸን ገንዘብ ጌታ ሆኖብናል በኢየሱስ ስም እያልን ነፍስን አሳደናል - ማረን ይቅር በለን ማጉረምረምን ትተን ስለቅጣታችን ወዳንተ እንመለስ ይቅር መንገዳችን - ማረን ይቅር በለን ወደላይ ይነሳ ልባችን ከእጃችን ደመናትን ይለፍ ይሂድ ልመናችን - ማረን ይቅር በለን መሪር ሃዘን ሊሆን ኢካቦድ ተወልዶ ካንተ ፊት ሲጠፋ ሰው ሃጢያት ተላምዶ - - ማረን ይቅር በለን እያየን ሲርቀን ክብርህ ከፊታችን ዛሬ ላይ መልሰን አንተው ነህ ተስፋችን - - ማረን ይቅር በለን