Loading
አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ ወደ ፡ ምድረበዳ ፡ አባብላታለሁ ሚስጥሬን ፡ ለመግለጽ ፡ እኔ ፡ እለያታለሁ ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ ለበጐ ፡ ነው ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ በፍቅርህ ፡ ነው ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ ወደኽኝ ፡ ነው ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ መርጠኽኝ ፡ ነው ጥያቄ ፡ የለኝም ፡ መልስ ፡ አንተ ፡ ሆነኸኝ በማ እ፡ በሉ ፡ ምርሃል ፡ መኖር ፡ አስለመድኸኝ ቢያይልም ፡ ወጀቡ ፡ ቢቆጣም ፡ ነፋሱ ይታዘዛል ፡ ሁሉም ፡ ለአንተ ፡ ለንጉሡ ለእኔስ ፡ ሆኖልኛል ፡ ሃይልህን ፡ የማይበት የጠላቴ ፡ ወጥመድ ፡ ራሱ ፡ ሚያዝበት አብረኸኝ ፡ እስከ ፡ ሆንክ ፡ በመርከበ ፡ ላይ ለመልካም ፡ ይሆናል ፡ ክብርህን ፡ እማይበት አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ በዓይኖቸ ፡ ማየው ፡ በፊቴ ፡ ያለው እያንዳንዱን ፡ ነገር ፡ ፈቅደህለት ፡ ነው በዙፋንህ ፡ ሆነህ ፡ ትመለከታለህ ግድ ፡ ይለኛል ፡ ለኔ ፡ ልጄ ፡ ነች ፡ ትላለህ እኔ ፡ ባይገባኝም ፡ ማልፈውን ፡ ጐዳና የምሕረት ፡ እጆችህ ፡ አቅፈውኛልና ዛሬም ፡ አምንሃለሁ ፡ አዎ ፡ እንደገና ነፍሴ ፡ አረጋግጣለች ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ጌታ አትተወኝም ፡ ጌታ አንተን ፡ ለሚወዱ ፡ በአንተ ፡ ለተጠሩ ለበጐ ፡ ይሆናል ፡ የሚያልፉበት ፡ ሁሉ አትደክም ፡ አትተኛ ፡ አትዝል ፡ አትረሳ ታውቀሃል ፡ እንደሆንክ ፡ መልካሙ ፡ እረኛ በበትህ ፡ የኖረ ፡ በአንተ ፡ የተመካ አያፍርም ፡ ዘለዓለም ፡ ለአንድም ፡ ደቂቃ ግን ፡ አስቀምጠኸው ፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ በከፍታ ከሞገስህ ፡ ጠግቦ ፡ ይኖራል ፡ በግርማ አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.