Loading
Singer
ልጄ ፡ ሆይ ፡ ህጌን ፡ አትርሳ ፡ ልብህም ፡ ት እዛዛቴን ፡ ይጠብቅ ብዙ ፡ ዘመናትና ፡ ረጅም ፡ ዕድሜ ቃልህን ፡ ሰምቻለሁ ፡ ድምፅህን ፡ ሰምቻለሁ ምክርህን ፡ ሰምቻለሁ ፡ ሰምቻለሁ ፍሬ ፡ እንዳታጣብኝ ፡ ግን ፡ እፈራለሁ የሚወድህ ፡ ቃልህን ፡ ይጠብቃል ትእዛዛትህን ፡ በመንገዱ ፡ ያረጋል ድምፅህን ፡ ሰምቼ ፡ ጌታ ፡ ካልታዘዝኩኝ የታለ ፡ ፍቅሬ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ምክርህ ፡ ካልተቀየርኩኝ ከክፉ ፡ ሃሳቤም ፡ ካልተመለስኩኝ መልኬን ፡ ብቻ ፡ አይቶ ፡ መሄድ ፡ ይሆንብኛል ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል ቁጣህም ፡ ሳይብስ ፡ ቅጣት ፡ ሳይመጣ ፡ ጌታ ፡ መልሰኝ ፡ ጨርሼ ፡ እንዳልወጣ ያኔ ፡ በረከት ፡ ፍሬ ፡ ይበዛልኛል በመታዘዜ ፡ መውደዴ ፡ ይታያል የልቤ ፡ መሻት ፡ የውስጥ ፡ ጥማቴ አክብሬህ ፡ መኖር ፡ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ፀጋህን ፡ እሻለሁ ፡ በዚም ፡ ደግሜ