Loading
Singer
ብዙ ፡ አመታት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ስትወጣ ፡ ስትወርድ ስለ ፡ ስሜ ፡ ስትሰደብ ፡ ስትመታ ፡ ስትዋረድ ልመጣ ፡ ስል ፡ ትንሽ ፡ ሲቀር ፡ ልጐበኝህ ልፋትህን ፡ ከንቱ ፡ አድርገህ ፡ ምነው ፡ ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ የድካምኽን ፡ የልፋትህን እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን እንደጀመርክ ፡ ብትጨርስ ፡ ያን ፡ ፍቅርህን ነፍሳት ፡ ለማዳን ፡ የነበረህን ፡ ጥማትህን ስትዘምር ፡ ስትጨልይ ፡ ጊዜህን ፡ ሰጥተህ ልሸልምህ ፡ ልመጣ ፡ ስል ፡ ምነው ፡ ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ የድካምኽን ፡ የልፋትህን እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን የጸለይከውን ፡ ጸሎትህን ፡ ልመናህን ላብሰው ፡ ስል ፡ ያነባኸውን ፡ እንባህን በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ልጄ ፡ ብዬ ፡ ስጠራህ ከቦታ ፡ አጣሁ ፡ እጄን ፡ ስዘረጋልህ አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ የድካምኽን ፡ የልፋትህን እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ የዘለልከው ፡ የወጣኸው እንደ ፡ ቃዬል ፡ ፍቅሬን ፡ ኃይሌን ፡ የቀመስከው እኔ ፡ ነበርኩኝ ፡ ውበትና ፡ ደም ፡ ግባትህ ልመጣ ፡ ስል ፡ ይሄን ፡ ረስተህ ፡ ምነው ፡ ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ የድካምኽን ፡ የልፋትህን እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን