Loading
Singer
ህልውናህን ፡ ሳጣው ፡ ከጐኔ ክብርህን ፡ ማየቱ ፡ ሲሳነው ፡ ዓይኔ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሲርቀኝ ፡ ከእኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ ሰጋለሁ ፡ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሰጋለሁ ወደ ፡ ጉድጓድ ፡ የሚወርዱትን ፡ መስላለሁ ሆሆ ፡ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ ስትደበቀኝ ፡ ሲሰወር ፡ ፊትህ ዝግ ፡ ሲሆንብኝ ፡ ደጅ ፡ በብረት ማን ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ በማን ፡ ልመካ ኃይሌም ፡ ጉልበቴ ፡ ፊትህ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x) አትሰወርብኝ ፡ አትደበቀኝ ሰምተህ ፡ እንዳልሰማ ፡ አትሁንብኝ አትሰወርብኝ ፡ አትደበቀኝ አይተህ ፡ እንዳላየ ፡ አትሁንብኝ (፪x) ህልውናህን ፡ ሳጣው ፡ ከጐኔ ክብርህን ፡ ማየቱ ፡ ሲሳነው ፡ ዓይኔ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሲርቀኝ ፡ ከእኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ ሰጋለሁ ፡ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሰጋለሁ ወደ ፡ ጉድጓድ ፡ የሚወርዱትን ፡ መስላለሁ ሆሆ ፡ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ