Loading
Singer
ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x) ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል ቃልህ ፡ እጅግ ፡ ጣፋጭ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ወለላ ሰላም ፡ ይሰጠኛል ፡ በልቤ ፡ እየሞላ ሰይፍህ ፡ ነውሬን ፡ ከላይ ፡ አስወግዶ በቃልህ ፡ አስዋብከኝ ፡ ልብህ ፡ ልቤን ፡ ወዶ (፪x) አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x) ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ አስተዋይ ፡ አረገኝ ፡ አስተዋዩ ፡ አባቴ የፈገግታዬ ፡ ምንጭ ፡ የደስታ ፡ ምክንያቴ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ ጌታዬ ፡ ደምህ ፡ ነው ፡ የልጅነት ፡ መብቴ (፪x) አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x) ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ