Loading
ምህረትህና ፡ ቸርነትህ ፡ በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ይከተሉኛል እለት ፡ እለት ፡ ክቡር ፡ ደሙ ፡ ይሸፍነኛል ፡ ይጠብቀኛል ሃሌሉያ ፡ ቤትህ ፡ ያገቡኛል ታማኙ ፡ እጅህ ፡ መቼ ፡ ይጥላል ታማኙ ፡ እጅህ ፡ ቤት ፡ ያደርሳል (፪x) ሃሌሉያ ፡ ቤትህ ፡ ያገቡኛል ዝም ፡ ዝም ፡ አትበል ፡ ነፍሴ ፡ ትለኛለች የአምላኳን ፡ ውለታ ፡ ሁሌም ፡ ታስባለች (፪x) እንዴት ፡ የምን ፡ ዝም ፡ ዝም ፡ ዝምታ በልቤ ፡ ለሞላው ፡ ጌታ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ልመስክርልህ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ ማያውቅ ፡ አለ ፡ እንዴ ሃሌሉያ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ልውደድ ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) ሃሌሉያ ፡ በጣም ፡ እወድሃለሁ ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) ሃሌሉያ ፡ በጣም ፡ እወድሃለሁ እንዴት ፡ የምን ፡ ዝም ፡ ዝም ፡ ዝምታ በልቤ ፡ ለሞላው ፡ ጌታ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ልመስክርልህ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ ማያውቅ ፡ አለ ፡ እንዴ ሃሌሉያ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ልውደድ ያለፈው ፡ ዘመኔ ፡ አለፈ ፡ አለፈ ዳግመኛ ፡ ላላየው ያለፈው ፡ ኑሮዬ ፡ አለፈ ፡ አለፈ ዳግመኛ ፡ ላላየው ቀሪውን ፡ ዘመኔን ፡ ባርከው ፡ ባርከው የአንተው ፡ ለአንተው ፡ አድርገው ያለአንተ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንልኝም ከእንግዲህ ፡ እንካ ፡ ተቆጣጠረኝ ከእንግዲህ ፡ እንካ ፡ እንካ ፡ ጌታ ፡ ተቆጣጠረኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.