Loading
Singer
ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x) አመልክሃለሁ ፡ በቀንም ፡ በሌሊትም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ (፪x) የህይወቴ ፡ ጌታ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ተስፋ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም ከአንተ ፡ ውጬ ፡ ሌላ ፡ የለም ፡ አዎ ፡ ሌላ ፡ የለም አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፡ አዎ ፡ ለዘለዓለም (፪x) እስከዛሬ ፡ ስኖር ፡ በዚህች ፡ ምድር አንድም ፡ አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x) ሁሉ ፡ ሲይዙት ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ ሲጨብጡት ፡ እንደ ፡ ጉም ፡ ነው ኢየሱስ/ጌታ ፡ በአንተ ፡ ማረፍ ፡ ግን ፡ እጅግ ፡ መታደል ፡ ነው (፪x) እገባለሁ ፡ ወደውስጥ ፡ አንተ ፡ ወዳለህበት እመጣለሁ ፡ በደስታ ፡ ለአንተ ፡ ልገዛ ፡ ጌታ እገባለሁ ፡ ወደውስጥ ፡ አንተ ፡ ወዳለህበት (ወዳለህበት) እመጣለሁ ፡ በደስታ ፡ ለአንተ ፡ ልገዛ ፡ ጌታ (እየሰገድኩ) እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (ለአንተ ፡ እገዛለሁ) ለአንተ ፡ እገዛለሁ እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) ፡ እያመለኩ ፡ (አንተን ፡ አነግሳለሁ) አንተን ፡ አነግሳለሁ እየሰገድኩ (ጌታዬ) ፡ እያመለኩ (ለአንተ ፡ እኖራለሁ) ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (አንተን ፡ አንተን) አንተን ፡ አከብራለሁ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (ለአንተ ፡ እገዛለሁ) ለአንተ ፡ እገዛለሁ እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) ፡ እያመለኩ ፡ (ጌታ ፡ አነግሻለሁ) አንተን ፡ አነግሳለሁ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ