Loading
Singer
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ከሞት ፡ ይልቅ ፡ ብርቱ ፡ ነው ሕይወቴን ፡ እንደ ፡ መልሕቅ ፡ ያጸናው መልካሙን ፡ ተስፋ ፡ ያስያዘው በልቤ ፡ የሞላው ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x) ሳልወድህ ፡ ገና ፡ አንተ ፡ ወደድከኝ የሚረባኝን ፡ አንተ ፡ አስተማርከኝ ሳላውቅህ ፡ ገና ፡ አንተ ፡ አወቅከኝ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ነጥቀህ ፡ አስጣልከኝ እንዲህ ፡ ላረከው ፡ ምን ፡ አስቀራለሁ በምላሽ ፡ ይኸው ፡ እዘምራለሁ (፫x) አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ከሞት ፡ ይልቅ ፡ ብርቱ ፡ ነው ሕይወቴን ፡ እንደ ፡ መልሕቅ ፡ ያጸናው መልካሙን ፡ ተስፋ ፡ ያስያዘው በልቤ ፡ የሞላው ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x) በልቤ ፡ ፈሶ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ጠራርጐ ፡ ያወጣል ፡ የክፋትን ፡ ዘር ግንዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መሰረት የሕይወት ፡ ራስ ፡ የተፈጠርኩበት ሁሉ ፡ ከርሱ ፡ ነው ፡ የሆነው ፡ ሕይወት ትምክት ፡ የለኝም ፡ የምመካበት (፫x) ፍቅርህ ፡ ገዢ ፡ ነው ፡ አያውቅም ፡ ክፋት ፍጥረትን ፡ ማርኮ ፡ ያንበረከከ ሕልውናህ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ባህሪህ ፀንቶ ፡ ሚቀጥል ፡ ከሁሉ ፡ ሚበልጥ ሕግን ፡ ፈጽሞ ፡ የጠቀለለው ፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በደል ፡ የማይቆጥረው (፫x)