Loading
Singer
ሌት ፡ ከቀን ፡ ደክሜ ፡ ስምህን ፡ ለማስከበር ብዙ ፡ ተጉዣለሁ ፡ ወንጌልን ፡ ለማብሰር አምላኬ ፡ እንዲህ ፡ ይላል ፡ እያልኩኝ ፡ ተግቼ ድምጼ ፡ እስከሚሰልል ፡ ነፍሳት ፡ ተጣርቼ አንዳንዴ ፡ ጉዳትን ፡ አንዳንዴም ፡ ማጣትን ስለ ፡ ስሙ ፡ ችዬ ፡ በለቅሶ ፡ ያለፍኩትን ሁሉንም ፡ ዘርዝሬ ፡ ታሪኬን ፡ ስገታ አምላኬ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ በረቂቅ ፡ ዝግታ አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አድምጠኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጥማት ቀዳሚ ፡ ትዕዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት ነፍስን ፡ የሚጠግን ፡ የሚጣፍጥ ፡ ዜና ሕዝብህን ፡ የሚያንጽ ፡ ለነፍስ ፡ የሚስማማ የጠለቀ ፡ ሚስጢር ፡ ቅኔ ፡ እንደባለቅን የዜማውን ፡ ስንኝ ፡ በንጹህ ፡ አርቅቄ ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ በቤትህ ፡ ዘመርኩኝ ሕዝብህ ፡ እልል ፡ እስኪል ፡ ስምህን ፡ አስከበርኩኝ ብዬ ፡ ብዘረዝር ፡ ያማላሁኝ ፡ መስሎኝ ያላስተዋልኩትን ፡ አምላኬ ፡ አሳስበኝ አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አትሞኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጉዳት ቀዳሚ ፡ ትዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት ደጋግሞ ፡ በመጾም ፡ ሥጋዬን ፡ ጐድቼ ጉልበቴ ፡ እስኪሻክር ፡ በጸሎት ፡ ተግቼ አጣሁ ፡ ብመለከት ፡ ከዋና ፡ ቆርሼ ህመም ፡ ለጐበኘው ፡ በጸሎት ፡ ደርሼ ለእምነቱ ፡ ተጋዳይ ፡ ተብዬ ፡ እስክጠራ ስላንተ ፡ ተሰደድኩ ፡ ከሐዋርያት ፡ ጋራ ብዬ ፡ የኔንም ፡ ታሪክ ፡ እንደ ፡ ደመደምኩኝ ነፍስ ፡ የምትመረምር ፡ አንዴ ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁኝ አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አድምጠኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጉዳት ቀዳሚ ፡ ትዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት