Loading
Singer
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x) ጸሃፊ ፡ መች ፡ ጠፍቶ በምድር ፡ ላይ ፡ ምሁር ፡ ሰው የአንተን ፡ ታላቅነት ፡ ጀምሮ ፡ አይጨርሰው መች ፡ አንዲህ ፡ ይቀላል ፡ ስለአንተ ፡ ቢባል ፡ ቢባል ቢጻፍልህ ፡ ተጀመሮ ፡ ቀለም ፡ ያልቃል እኔ ፡ ግን ፡ አድናቆቴን ፡ ለአንተ ባለኝ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ማወደሴን ፡ ማክበሬን ፡ አልተውም ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪሰማ ጌታዬ ፡ ጌታዪ ፡ ነህ ፡ እያለኩ ቤትህ ፡ ቆሜ ፡ እንጓደዳለሁ ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ እንደአንተ ፡ የት ፡ አገኛለሁ አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x) ስለአንተ ፡ ክብር ፡ ስልጣን ፡ ሞገስ ፡ ማንነት እየተረከ ፡ ነው ፡ ይኼ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት ይህ ፡ ነው ፡ እስከዛሬ ፡ ከፍጥረት ፡ ጀምሮ አላለቀበትም ፡ ስለአንተ ፡ ተናግሮ አቤት ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ እሄ ሁሉ ፡ ምሥጋናና ፡ ስግደት ያለማቋረጥ ፡ ያጐርፍልሃል ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ከያለበት እኔም ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ ለአንተ ፡ ዛሬ ፊትህ ፡ ለማቅረብ ፡ ምሥጋና ጌታዬ ፡ ጌታዪ ፡ ነህ ፡ እያልኩኝ ልቀኝልህ ፡ እንደገና አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x) እስከ ፡ ዛሬ ፡ ስለአረክልኝ ፡ ውለታ አቀርብልህ ፡ ነበር ፡ ምሥጋናና ፡ እልልታ ስለአረክልኝ ፡ አይደለም ፡ ምቀኝልህ ስለደነቀኝ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ማንነትህ ተገረምኩ ፡ አድናቆት ፡ ያዘኝ ፡ በአንተ ማንነትህን ፡ አውቄ እስቲ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ልበል በእግሮችህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ቃላት ፡ ያንሰኛል ፡ ለመግለጽ ፡ የአንተን ማንነትህ ፡ ወደር ፡ የለው . (1) . ፡ ፍቅርህ ስምህ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)