Loading
ለእኔ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x) መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ ነበርኩ መጣልኝ ፡ ሲሳይ አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ እንደዚህ ፡ የሚያደርገው ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x) ከላይ ፡ ከሰማይ ፡ የባሪያን ፡ መልክ ፡ ይዞ በእኔ ፡ በኃጢአተኛዋ ፡ በፍቅር ፡ ተይዞ ካለሁበት: አዘቅት፡ ከሞት ፡ ሊያወጣኝ እርሱ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ነጻ ፡ ነሽ ፡ አለኝ አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ እንደዚህ ፡ የሚያደርገው ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x) በዚያ ፡ በጐልጐታ ፡ በቀራኒዮ ፡ ላይ ከቶ ፡ መች ፡ አፈረ ፡ እርቃኑ ፡ ሲታይ የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ተመታ ፡ በደዌ እርሱ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ይኸው ፡ ዳንኩኝ አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ እንደዚህ ፡ የሚያደርገው ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x) ወርዱና ፡ ስፋቱ ፡ የማይለካው ጥልቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ ፡ ወሰን ፡ የሌለው የልቤ ፡ አይወጣም ፡ ብዙ ፡ ቃል ፡ ደርድሬ ሳመሰግን ፡ ብውል ፡ በመልካም ፡ ዝማሬ ለእኔ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x) መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ ነበርኩ መጣልኝ ፡ ሲሳይ አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ እንደዚህ ፡ የሚያደርገው ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.