Loading
Singer
ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ነፍሱን ፡ አሳልፎ እስከ ፡ መስቀል ፡ ታዟል ፡እራሱን ፡ አዋርዶ እንዲህ ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ከወዴት ፡ ተሰምቷል? በእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ፍቃድ ፡ በኢየሱስ ፡ ተገልጧል (፪x) ፍቅር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነው ስራው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x) የኃያላን ፡ ጉልበት ፡ ዝናው ፡ ሁሉ ፡ ያልፋል ክብሩ ፡ ከበሬታው ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ይቀራል የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ በግርማ ፡ በክብር በኃይል ፡ በሞገሱ ፡ ፀንቶ ፡ የሚኖር (፪x) ኃያል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ኃያል ፡ ነው ስራው ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፊት ፡ አይቶ ፡ አያደላ ፡ ለሁሉ ፡ ነው ፡ ወዳጅ የልብ ን ፡ የሚረዳ ፡ እውነተኛ ፡ ፈራጅ ስራው ፡ በትክክል ፡ ሚዛኑ ፡ እውነት ፡ ነው በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ በስራው ፡ ፃድቅ ፡ ነው (፪x) ፃድቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፃድቅ ፡ ነው ስራው ፡ ፃድቅ ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ፃድቅ ፡ ነው (፪x) ሌላ ፡ ምን ፡ እንበልህ ፡ ምን ፡ እናቅርብ በፊትህ ፡ ከማዜም ፡ ከመቀኘት ፡ በቀር (፬x) ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ይኸው ፡ ዝማሬ ፡ አምልኮ ስግደት ፡ ዕልልታ ፡ ክብር ፡ አሜን ፡ ይሁን (፪x)