Loading
Singer
ተጨነቀ ፡ ተሰቃየ አፉን ፡ አልከፈተም ፡ ዝም ፡ አለ ታረደ ፡ እንደ ፡ በግ የእኔን ፡ ነፍስ ፡ ሊታደግ የእኔን ፡ ነፍስ ፡ ሊታደግ ተጨነቀ ፡ ተሰቃየ አፉን ፡ አልከፈተም ፡ ዝም ፡ አለ ታረደ ፡ እንደ ፡ በግ የእኔን ፡ ነፍስ ፡ ሊታደግ የእኔን ፡ ነፍስ ፡ ሊታደግ ሁሌ ፡ አስባለሁ ፡ ፍቅሩን ሁሌ ፡ እስበዋለሁ ፡ ፍቅሩን የኢየሱሴን ፡ የእውነተኛውን ሁሌ ፡ አስባለሁ ፡ ፍቅሩን ሁሌ ፡ እስበዋለሁ ፡ ፍቅሩን የኢየሱሴን ፡ የእውነተኛው የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ በደዌ ፡ ተመታ ፡ ፍቅር ፡ ነው እንደ ፡ በግ ፡ ተነድቶ ፡ እንዳልሆነ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ነው እሾሁን ፡ ጅራፉን ፡ እለፋውን ፡ ቻለ ፡ ፍቅር ፡ ነው መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ እያለ ፡ ለእኔ ፡ ነው የእግዚአብሔርን ፡ ፈቃድ ፡ በእጁ ፡ ሊከውን ከነፍሱ ፡ ድካም ፡ ሊያይ ፡ ብርሃንን ታግሶታል ፡ አቤት ፡ ኢየሱሴ በጸሎት ፡ በእንባ ፡ ታክብረው ፡ ነፍሴ ጌታ ፡ እሰከሞቱ ፡ ሰው ፡ ወደደ ጌታ ፡ እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ሰው ፡ ወደደ ይቅር ፡ በላቸው ፡ በሎ ፡ እየማለደ ጌታ ፡ እሰከሞቱ ፡ ሰው ፡ ወደደ ጌታ ፡ እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ሰው ፡ ወደደ ይቅር ፡ በላቸው ፡ በሎ ፡ እየማለደ ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ እያለ ፡ ተጣራ ፡ ፍቅር ፡ ነው እንደማይችል ፡ እራሱን ፡ ባዶ ፡ አደረገና ፡ ለኔ ፡ ነው እንደ ፡ ወንጀለኛ ፡ እየተዘለፈ ፡ ፍቅር ፡ ነው ስለ ፡ ሃጥያተኞች ፡ ነፍሱን ፡ አሳለፈ ፡ ለኔ ፡ ነው የእግዚአብሔርን ፡ ፈቃድ ፡ በእጁ ፡ ሊከውን ከነፍሱ ፡ ድካም ፡ ሊያይ ፡ ብርሃንን ታግሶታል ፡ አቤት ፡ ኢየሱሴ በጸሎት ፡ በእንባ ፡ ታክብረው ፡ ነፍሴ