Loading
Singer
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ የትውልድ ፡ መጠጊያ የፍጥረት ፡ መጋቢ ፡ ድጋፍ ፡ መሸሸጊያ ልጅህን ፡ በመስጠት ፡ ፍቅርን ፡ የተገበርክ ዓለሙን ፡ በሙሉ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድክ ፍቅር ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ይቅር ፡ ባይ ፡ የምትምር እልፍ ፡ ነው ፡ ቸርነትህ አይቆጠር (አይነገር )፡ ማጽናናትህ(፪x) ፍቅር ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ እያልኩ ፡ ባዜምልህ ደግሞ ፡ በአዲስ ፡ ምሕረት ፡ ታስደንቀኛለህ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እልሃለው ፡ እጠራሃለው ፡ ደግሜ ልዩ ፡ ነው ፡ አወዳደድህ ፡ ላዚምልህ ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነህ እንዴት ፡ ያለህ ፡ መሃሪ(ወዳጅ) ፡ ነህ (፪x) የዘላለም ፡ አምላክ ፡ የትውልድ ፡ መጠጊያ የፍጥረት ፡ መጋቢ ፡ ድጋፍ ፡ መሸሸጊያ ልጅህን ፡ በመስጠት ፡ ፍቅርን ፡ የተገበርክ ዓለሙን ፡ በሙሉ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድክ ፍቅር ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ይቅር ፡ ባይ ፡ የምትምር እልፍ ፡ ነው ፡ ቸርነትህ አይቆጠር (አይነገር )፡ ማጽናናትህ(፪x) የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ ፍቅርን ፡ ለተጠማ የምታለመልም ፡ ነፍስን ፡ የምታረካ አውርቼ ፡ አውርቼ ፡ አልጠግብም ፡ አይገልጽህም ፡ ቃላቴ ደግነትህን ፡ ብዘምር ፡ አልገልጸውም ፡ በዚህ ፡ አንደበቴ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነህ እንዴት ፡ ያለህ ፡ መሃሪ(ወዳጅ) ፡ ነህ (፪x)