Loading
አልሳሳ ፡ በልጅህ ፡ ሲመጣ አልቀስ ፡ የቁጣህን ፡ መጠን እኔ ፡ ላጠፋሁት ፡ ክፉ ፡ ላደረኩት ሰዋኸው ፡ ቅዱሱን ፡ ሃጥያት ፡ ያላየውን የዓለም ፡ ፍርድን ፡ ሲወስድ ፊትህን ፡ ያዞርከው አስበኸኝ ፡ ነው ፡ ወደኸኝ ፡ ነው መርጠኸኝ ፡ ነው ፡ አውቀኸኝ ፡ ነው ራርተህልኝ ፡ ነው ፡ አዝነህልኝ ፡ ነው ሳስተህልኝ ፡ ነው ፡ አፍቅረኸኝ ፡ ነው ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ደግ ፡ ነህ ፡ ክፉ ፡ ላሰበብህ ትራራለህ ፡ ልቡን ፡ ላዞረብህ እየዘበቱብህ ፡ እያሾፉብህ ስራቸውን ፡ አያውቁም ፡ የሚያደርጉትን ምሕረት ፡ አርግላቸው ፡ ብለህ ፡ የጸለይክ ልዩ ፡ ነህ ፡ የተለየህ አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ አቤት ፡ ምሕረትህ ውብ ፡ ነህ ፡ የተለየህ አቤት ፡ በጐነትህ ፡ አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ምሕረትህ ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ አዲስ ፡ ነው ፡ በየጥዋቱ ሃጥያትን ፡ ለሰሩ ፡ ለበደሉ እጅህ ፡ ይዘረጋል ፡ ለያንዳንዱ የትላንቱን ፡ እረስተህ ፡ እንዳጠፉ ምሕረትህ ፡ ብዙ ፡ በጐነትህ ፡ ብዙ ፍቅርህ ፡ ብዙ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዙ ትህትናህ ፡ ብዙ ፡ ርህራሄህ ፡ ብዙ ትዕግሥትህ ፡ ብዙ ፡ መውደድህ ፡ ብዙ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.