Loading
አዝ፦ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x) የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x) ፍቅርን ፡ የተራበ ፡ ፍቅርን ፡ የተጠማ ፡ ከውስጡ ፡ ካንጀቱ ስለፍቅር ፡ አይነት ፡ ቢሰማ ፡ አይሰለቸው ፡ ተርቧል ፡ ከእውነቱ አውቋል ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ የፍቅርን ፡ መቋጫ ፡ የመጨረሻውን ከመቃብር ፡ ድረስ ፡ የገባውን ፡ ኪዳን ፡ ውሉን ፡ ማስረጃውን ግን ፡ ደግሞ ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ መቃብር ፡ ያለፈ ፡ ፍቅሩ ፡ ያልተሸነፈ በፍቅር ፡ ተይዞ ፡ ያለምክንያት ፡ ወርዶ ፡ ከመቃብር ፡ ማዶ ተቀብሮ ፡ ያልቀረ ፡ ጥሶ ፡ የተሻገረ ፡ ጭራሹን ፡ ያረገ ሞቶ ፡ የተነሳ ፡ ሃዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ በምድር ፡ ያለ ፡ ሁሉ ፡ ቢጠራ ፡ ቢጠራ ፡ ለችግረኛ ፡ ሰው ፡ ምኑ ፡ ነው ፡ የሚራራ ሞትህ ፡ ለኔ ፡ ይሁን ፡ እያለ ፡ ሰው ፡ ውሸቱን ፡ በስራ ፡ ያሳየ ፡ አግኝተናል ፡ አንዱን ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ፍቅሩን ፡ የገለጠ ፡ ቢጠቀስ ፡ አንድ ፡ የለም ፡ ከጌታ ፡ የበለጠ ከጌታ ፡ የበለጠ (፪x) አዝ፦ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x) የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x) በቁሙ ፡ የተጠላ ፡ የተኮራረፈ ፡ የሚዘጋበት ፡ በር የሞቱ ፡ ቀን ፡ ደግሞ ፡ ያዙኝ ፡ ልቀቁኝ ፡ ሲል ፡ አብሮ ፡ ለመቀበር መውደዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በእንጉርጉሮ ፡ ዜማ ፡ አልቃሽ ፡ አስጠርቶ የአርባው ፡ እለት ፡ ደግሞ ፡ ሙሾ ፡ ሲያወጣለት ፡ ሐውልት ፡ አሰርቶ አቤት ፡ ሲዋደዱ ፡ ይላል ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ነገሩ ፡ ያልገባው ይደነቃል ፡ ብሎ ፡ የነዚህስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እስከ ፡ መቃብር አልሰማ ፡ የኔን ፡ ነገር ፡ ወዶኝ ፡ ስለሞተ ፡ ነፍሱን ፡ ስለሰጠ የኔ ፡ ብርቱ ፡ አፍቃሪ ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ሄዷል ፡ ወደሰማይ በፍቅር ፡ እስራት ፡ ገመድ ፡ የገመደ ፡ ከሰው ፡ ጋር ፡ ሊወዳጅ ፡ ከላይ ፡ የወረደ አብሮ ፡ ሄዶ ፡ ሄዶ ፡ ጫፍ ፡ እየደረሰ ፡ አይሰናበትም ፡ እየተመለሰ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ቢገለባብጠው ፡ ይምጣና ፡ ይወራረድ ፡ ጌታዬን ፡ አይበልጠው ጌታዬን ፡ አይበልጠው (፪x) አዝ፦ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x) የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.