Loading
Singer
እንደበግ ፡ ሲነዳ ፡ አሁን ፡ አልከፈተም ወስደው ፡ ሲያንገላቱት ፡ አንዳች ፡ አልመለሰም (፪x) አስጨነቁት ፡ በጅራፍ ፡ ገረፉት በአደባባይ ፡ እርቃኑን ፡ ሰቀሉት ቤዛ ፡ ሆነ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ስለእኔ ፡ ተመታ ፍቅር ፡ ጐልጐታ ፡ ላይ ፍቅር ፡ ቀራኒዮ ፡ ላይ (፪x) እዩት ፡ እየሲሴን ፡ እዩት ፡ ስቃዩ ፡ ሲያይል እዩት ፡ አባብዬን ፡ እዩት ፡ ሲቃዩ ፡ ሲያይል ስቃዩ ፡ ሲያይል (፬x) ለእኔ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ መንከራተቱ ለእኔ ፡ ነው ፡ ስቃይን ፡ ማየቱ ለእኔ ፡ ነው ፡ ሲዘባበቱበት ለእኔ ፡ ነው ፡ የበዛው ፡ ትዕግሥቱ ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ያለው ለእኔ ፡ ነዋ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበው ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ህመሜ ፡ ያመመው ለእኔ ፡ ነዋ ፡ በጦር ፡ የተወጋው ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x) አባት ፡ ሆይ ፡ ፈቃድህ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ ብሎ መራራውን ፡ ጽዋ ፡ ጠጣው ፡ ተንጠልጥሎ (፪x) አፈረሰው ፡ የጥሉን ፡ ግድግዳ ፡ አስታረቀን ፡ እኛን ፡ ከአብ ፡ ጋራ ኢየሱሴ ፡ ጣልቃ ፡ ገብቶ ፡ አንድ ፡ አደረገን ፡ ሞቶ ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ብሎ ፡ የዋተተው ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ጀርባውን ፡ በጅራፍ ለእኔ ፡ ነዋ ፡ የተተለተለው ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x) የድካሙን ፡ ዋጋ ፡ ፍሬውን ፡ ሊያይ ታገሰ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሲቀበል ፡ ስቃይ (፪x) የተናቀ ፡ ደግሞም ፡ የተጠላ የህማም ፡ ሰው ፡ መሰለ ፡ ተላላ በቁስሎቹ ፡ ተፈውሻለሁ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x)