Loading
Singer
የሕይወት ፡ መገኛ ፡ የዘለዓለም ፡ ውረት ፈቃድህን ፡ ማድረግ ፡ ለሀሳብህ ፡ መወገድ ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ አስቀድመህ ፡ ያኔ የልጅህን ፡ መልክ ፡ እንድንሰው ፡ ነው ፡ ውሳኔ ከታናሽነቴ ፡ ከብላቴንነት የመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር የለየኸኝ ፡ ጌታ ፡ በጐና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፍፁም ፡ የሆነው ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ ዘንድ ፡ በሕይወቴ ጣልቃ ፡ ግባ ፡ በእያንዳንዱ ፡ ነገሬ የሚረባኝ ፡ የሚበጀኝን ታውቅልኝ ፡ አይደል ፡ አባቴ (፪x) ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ በሕይወቴ (፫x) አላማህ ፡ ይፈፀም ፡ በሕይወቴ (፫x) ለእኔ ፡ ብዬ ፡ የምተወው ፡ (የምተወው) አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ የምሸሽገው ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ (ሰጥቻለሁ) ፈቃድህ ፡ እንዲፈፀም ፡ እወዳለሁ ችላለሁ ፡ ብዬ ፡ የምተወው አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ የምሸሽገው ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ (ሁሉን ፡ ለአንተ) ፡ ሰጥቻለሁ ፈቃድህ ፡ እንዲፈፀም ፡ እወዳለሁ የአንተ ፡ ሀሳብ የአንተ ፡ አላማ የአንተው ፡ ፈቃድ በዘመኔ ፡ ይፈፀም (፪x)