Loading
Singer
የሚቀጠቅጥ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ወጥቷል ፡ በጠላት ፡ ተከበሃል ክርስቲያን ፡ ተጠንቀቅ ፡ ዙሪያህን ፡ አስተውል ጉልበትህ ፡ አይላላ ፡ ጠንክረህ ፡ ተዋጋ ብድራትን ፡ አይተህ ፡ ያለልህን ፡ ዋጋ አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ በጦርነት ፡ ላይ ፡ መቁሰልም ፡ አለ ፡ ሞትም ፡ ቢሆን ፡ ጥቅም ፡ ነው ለጨለማው ፡ ገዢ ፡ እጅህን ፡ አትስጠው እስከ ፡ ሞትም ፡ ታመን ፡ ነፍስህን ፡ አታክብራት ለታመነው ፡ ፈጣሪ ፡ አሳልፈህ ፡ ስጣት አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ ባለጋራህ ፡ ዲያብሎስ ፡ ሊውጥህ ፡ እያገሳብህ ፡ ነውና ከድምፁ ፡ አትፍራ ፡ አባትህ ፡ አለና መንጋጋውን ፡ ዘግቶ ፡ ከአፉ ፡ ያስጥልሃል ከቶም ፡ እንደማይጥልህ ፡ በግልጽ ፡ ያሳየዋል አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ የውጊያው ፡ ጊዜ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ ወንድም ተነስ ፡ ተጋጠመው ፡ ድል ፡ ትነሳዋለህ በርትተህ ፡ ታገለው ፡ የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ጋሻ ፡ ይሆንሃል ለአገርህም ፡ አብቅቶ ፡ አክሊል ፡ ይሰጥሃል አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ