Loading
Singer
አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ) ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲዖል ፡ አዳንከኝ እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ (፪x) በቅጣት ፡ አለንጋ ፡ ብዙ ፡ ተገረፍኩኝ በገዛ ፡ ጥፋቴ ፡ ተጠቃሁ ፡ ቆሰልኩኝ እየተንገዳገድኩ ፡ አመጻዬ ፡ አስክሮኝ ገደል ፡ ከቶኝ ፡ ነበር ፡ ባትይዘኝ ፡ ገፍትሮኝ አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ) ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ የተፈጠርኩበት ፡ ምክንያቱ ፡ ገብቶኛል የመዳኔ ፡ ሚስጥር ፡ ተገልጦልኛል የአንተን ፡ አባትነት ፡ የልጅነቴን ፡ መብት በነጻ ፡ አገኘሁት ፡ የዘላለሙን ፡ ሀብት አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ) ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ ተታልዬ ፡ ኖርኩኝ ፡ ማንነቴ ፡ አባብሎኝ የመርጥኩት ፡ መንገድ ፡ የሚያዋጣኝ ፡ መስሎኝ ጊዜያዊው ፡ እርካታ ፡ ዓለም ፡ የምትሰጠው ላዩ ፡ ቢጣፍጥም ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ መርዝ ፡ አለው አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ) ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ እኔ ፡ የአለኝን ፡ አጥቶ ፡ ለሚንከራተተው ጽድቅ ፡ የኖረው ፡ መስሎት ፡ ለሚመጻደቀው የውስጥ ፡ አይኑ ፡ በርቶ ፡ ምነው ፡ እውነቱን ፡ ባየ ለክፋቱ ፡ ስትል ፡ እንደተሰቃየህ አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ) ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ (፫x)