Loading
Singer
እየሱስ ፡ የሚለው ፡ ስምህ ልዩ ፡ ትርጉም ፡ አለው ፡ ለእኔማ ስጠራው ፡ ስደጋግመው (፪x) መጽናኛዬ ፡ ነው ፡ መበርቻዬ ፡ ነው ፡ ሆ! ከፍታዬ ፡ ነው ፡ መነሻዬ ፡ ነው ፡ ሆ! መጽናኛዬ ፡ ነው ፡ መበርቻዬ ፡ ነው ፡ ሆ! ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ እየሱስ ፡ የሚለው እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ እየሱሴን እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ ከሞት ፡ ያዳነኝን ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝን ፡ የታደገኝን እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ እየሱስ (፬x) በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ሰላም በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ በረከት በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ኃይል በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ በእምነት ፡ ላለ ከሞት ፡ የሚያስጥል (አንተን) ደብቄ ፡ እንኳን፡ ፡ እራሴን ፡ ላሳይ (እየሱሴ) እንደው ፡ በአጋጣሚ ፡ ስምህን ፡ ሲያነሱ ፡ ሳይ (እየሱሴ) እንባ ፡ ይቀድማኛል ፡ ምሆነውን ፡ አጣለሁ (እየሱሴ) ፊቴ ፡ ድቅን ፡ ይላል ፡ ያረክልኝ ፡ ሁሉ (እየሱሴ) ቆሜ ፡ አደባባይ ፡ ገና ፡ አወራዋለው (እየሱሴ) በስምህ ፡ አላፍርም ፡ አለም ፡ ሁሉ ፡ ይስማው (እየሱሴ) ክብርስ ፡ ቢሉ ፡ የቱ ፡ ክብሬ ፡ ነው (እየሱሴ) ሁሉን ፡ ያገኘሁት ፡ ስምህን ፡ አምኜ ፡ ነው እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ እየሱሴን እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ ከሞት ፡ ያዳነኝን ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝን ፡ የታደገኝን በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ሕይወት በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ክብር በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ስልጣን በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ በእምነት ፡ ላለህ ታሪክ ፡ የሚቀይር ስምህ ፡ መፍትሄ ፡ ነው ፡ ለጥያቄ ፡ ሁሉ (እየሱሴ) ኧረ ፡ ማን ፡ አፍሯል ፡ በስምህ ፡ ተማምኖ (እየሱሴ) የስምን ፡ ጉልበት ፡ እኔም ፡ አውቀዋለው (እየሱሴ) በስምህ ፡ ታምኜ ፡ ያለፍኩት ፡ ስንቱን ፡ ነው (እየሱሴ) ለሞተው ፡ ነገር ፡ ሕይወት ፡ የሰጠህ (እየሱሴ) ያበቃው ፡ ነገር ፡ ተስፋ ፡ እየቀጠለ (እየሱሴ) ብዙዎች ፡ ሲጠፉ ፡ በሕይወት ፡ ያለሁት (እየሱሴ) ታምኜው ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ ብዬ ፡ ስለው ፡ ብዬ ፡ ስለው ሃይሌ ፡ ይታደሳል ፡ በረታለሁ ፡ በረታለሁ እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ ብዬ ፡ ስለው ፡ ብዬ ፡ ስለው ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እሻገራለሁ ፡ እጨምራለሁ