Loading
አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል (፪x) የበጐቹ ፡ መብዛት ፡ የላሞች ፡ መርባት የርሻው ፡ መብልን ፡ መስጠት ፡ ጐተራው ፡ መሙላት ሁሉም ፡ ተስብስቦ ፡ ቢከብ ፡ በዙሪያዬ የሚያህልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድል ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል መለኪያዬ ፡ ችግር ፡ እይደለም ፡ ማጣት ወይ ፡ አግኝቶ ፡ መክበር ፡ ምድራዊ ፡ ሃብት ለእኔ ፡ ሚበጀውን ፡ ከአንተ ፡ ይልቅ ፡ ማን ፡ ያውቃል ነፍስን ፡ ከመስጠት ፡ ሁሉስ ፡ መች ፡ ይበልጣል አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል ብሩንና ፡ ወርቁን ፡ ዓለምስ ፡ መች ፡ አታ እርካታ ፡ አጣች ፡ እንጂ ፡ ሰጭውን ፡ እረስታ ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ቢሞላ ፡ ቢጐድል ፡ ሆንክልኝ ፡ ደስታ አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል የጸሎቴ ፡ መልሱ ፡ ቢዘገይም ፡ ፈውሴ አንተ ፡ ካየህልኝ ፡ ተስማማሁ ፡ ኢየሱሴ በጨለማው ፡ ስልጣን ፡ ጭንቅላት ፡ ላይ ፡ ቁሜ እባርክሃለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገድል ፡ ብታድን ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.