Loading
Singer
አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት የእውነት ፡ አፍቃሪዬ (፪x) እናት ፡ ልጇን ፡ በጣር ፡ ትወልዳለች ወልዳ ፡ ጡት ፡ አጥብታ ፡ ታሳድጋለች በነፍሷ ፡ ላይ ፡ ድንገት ፡ ችግር ፡ ሲመጣ ወንዝ ፡ ውስጥ ፡ ጣለችው ፡ ሙሴን ፡ አውጥታ ግን ፡ አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰበሰበው በንጉሡ ፡ ቤት ፡ በተዓምር ፡ አሳደገው [1] ለሞት ፡ የተሰጠውን ፡ አነሳና በህዝቡ ፡ ላይ ፡ ሾመው ፡ ፀጋ ፡ አበዛና [2] አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት የእውነት ፡ አፍቃሪዬ አጋር ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ ተሰደደች አባት ፡ በልጁ ፡ ሲጨክን ፡ አየች ውኃም ፡ አለቀ ፡ ምንዎን ፡ ታጠጣው ጨነቃትና ፡ እራቀች ፡ ጥላው ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጥኖ ፡ መጣላት ውሃውን ፡ አየች ፡ ዓይኗን ፡ ከፍቶላት የሚያያትንም ፡ አየችውና ቤቷ ፡ መለሳት ፡ ተስፋ ፡ ሰጣትና [3] አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት የእውነት ፡ አፍቃሪዬ ወንድምንም ፡ አየሁት ፡ ጉድጓድ ፡ ሲጥል ለባርነትም ፡ ሲሸጥ ፡ ለባዕድ ፡ ወገን [4] ጌታ ፡ ግን ፡ ከግዞት ፡ አወጣውና በረከት ፡ ሆነ ፡ ዮሴፍ ፡ ነገሠና [5] ከሞተ ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ሆኖታል አለችው ፡ እህቱ ፡ አሁንስ ፡ ሸቶአል የኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ መቸ ፡ ያሸተዋል አላዛርን ፡ በድንቅ ፡ ከሞት ፡ ያስነሳዋል [6] አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት የእውነት ፡ አፍቃሪዬ እዮብ ፡ በቁስል ፡ እጅግ ፡ ተመቶ ሚስቱ ፡ እንኳን ፡ ጠልታው ፡ የሚቀርበው ፡ አጥቶ ክደህ ፡ ሙት ፡ ብላ ፡ ስታስቸግረው በሸክሙ ፡ ላይ ፡ ቀንበር ፡ ስትጭነው [7] አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከተፍ ፡ አለለት ምርኮውን ፡ በእጥፍ ፡ በእጥፍ ፡ መለሰለት [8] ሁሉንም ፡ በተራው ፡ አየሁት ፡ ቃኘሁት ግን ፡ ኢየሱሴን ፡ በልጦ ፡ አገኘሁት አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት የእውነት ፡ አፍቃሪዬ