Loading
Singer
አምልኮ (፫x) ፡ ይለኛል ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ መንፈስህ ፡ በእጥፍ ፡ አግኝቶኛል በል ፡ ዘምር (፫x) ፡ ይለኛል የሚወደኝ ፡ ጌታ ፡ ምህረት ፡ አድርጐልኛል ጠላት ፡ በዙሪያዬ ፡ መርዶ ፡ ሲያረዳኝ የጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ከላይ ፡ ሲያገኘኝ አስባለኝ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ አሃ ፡ አለሁ ፡ የሚል ፡ ጠፍቶ ጀግና ፡ የተባል ፡ አሃ ፡ ሁሉ ፡ አንገቱን ፡ ደፍቶ መጽሐፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ጌታዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ (፪x) ከአንተ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ንጉሥ በላዬ ፡ አልሾምኩም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥም ፡ ያለህ ፡ አንተ ፡ ነህ በፍጥረት ፡ አንደበት ፡ ትመሰገናለህ ጌታዬ ፡ ትመሰገናለህ (፪x) ሁልጊዜ ፡ ትመሰገናለህ (፪x) አልቅነትና ፡ ሥልጣናትን ፡ ገፎ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ ሁሉን ፡ አሸንፎ የሁሉ ፡ የበላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚገዛው እኔ ፡ የማመልከው ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x) አምልኮ (፫x) ፡ ይለኛል ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ መንፈስህ ፡ በእጥፍ ፡ አግኝቶኛል በል ፡ ዘምር (፫x) ፡ ይለኛል የሚወደኝ ፡ ጌታ ፡ ምህረት ፡ አድርጐልኛል ጠላት ፡ በዙሪያዬ ፡ መርዶ ፡ ሲያረዳኝ የጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ከላይ ፡ ሲያገኘኝ አስባለኝ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)