Loading
የኃያላን ፡ ቀስት ፡ ተሰባብሮ አለቅነትን ፡ ስልጣናትን ፡ ሽሮ በግርማው ፡ ያለ ፡ ሁሉን ፡ እየረታ ዛሬም ፡ ይገዛል ፡ የጌቶች ፡ ጌታ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው መንግሥቱም ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይረታው የተነሱበትን ፡ ሁሉንም ፡ ገልብጦ ብቻውን ፡ ይገዛል ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ጸንቶ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ጐርደድ ፡ እያለ ፡ ከጠላት ፡ ሰፈር ሺ ፡ ጦር ፡ ቢሰለፍ ፡ የማይበገር ድምጹ ፡ ነጐድጓድ ፡ የሚያስፈራራ ሁሉን ፡ የረታ ፡ ተራ ፡ በተራ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ነጉሰ ፡ ነገሥት ፡ ግርማዊ ፡ ተብለው በምድር ፡ ሲኖሩ ፡ ክብርን ፡ ተጋፍተው ዛሬ ፡ ተረስተው ፡ አፈር ፡ ሆነዋል ሞትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ተነስቷል አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው መንግሥቱም ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይረታው የተነሱበትን ፡ ሁሉንም ፡ ገልብጦ ብቻውን ፡ ይገዛል ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ በልጦ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.