Loading
Singer
ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ከሠማይ ፡ ወረደ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የሰው ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ራሱን ፡ አዋረደ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ ሆኖ ፡ በረት፡ ተወለደ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የዋህ ፡ ትሁት ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ በግ ፡ ታረደ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ፈራጅ ፡ በሌለበት ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የውርደት ፡ ሞት ፡ ሊሞት ፡ እንደወንጀለኛ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በደሙ ፡ ቢነከር ፡ ቀራንዮ ፡ ተራራ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና መቃብሩም ፡ ቢሆን ፡ ከአመፀኞች ፡ ጋራ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በሞተ ፡ ሰልስቱ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አይሰማ ፡ ሰምቶ ፡ ዓለም ፡ ደነገጠ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና መቃብሩን ፡ ከፈተ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈታ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ሞትን ፡ ድል ፡ አረገ ፡ የትንሳኤው ፡ ጌታ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አዝ፦ ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x) ተወዳዳሪ ፡ የለውምና አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x) የሞት ፡ መርዶ ፡ ሰምተው ፡ በሃዘን ፡ የተዋጡ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በትንሳኤው ፡ ብስራት ፡ ዕልልታ ፡ አቀለጡ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አጠፋነው ፡ ብለው ፡ የዘፈኑ ፡ ሁሉ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ትንሳኤውን ፡ ሲሰሙ ፡ ምድር ፡ ዋጪን ፡ አሉ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በኢየሱስ ፡ ሰፈር ፡ ዕልልታ ፡ ሲሰማ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በዲያብሎስ ፡ ሰፈር ፡ የሃዘን ፡ ጨለማ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ከማሪያም ፡ ጀምሮ ፡ እስከ ፡ ቶማስ ፡ ድረስ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በዐይን ፡ በማየት ፡ ደግሞም ፡ በመዳሰስ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ኢየሱስ ፡ መነሳቱን ፡ አረጋገጡልን ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ይህን ፡ ክቡር ፡ ታሪክ ፡ ፅፈው ፡ አስቀሩልን ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አምነን ፡ የተቀበልን ፡ እኛም ፡ ተነስተናል ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ሞትን ፡ እረግጠናል አዝ፦ ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x) ተወዳዳሪ ፡ የለውምና አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x) የኢየሱስ ፡ ጌትነት ፡ በዚህ ፡ አላበቃም ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ገና ፡ ይቀጥላል ፡ ታሪክ ፡ አልተዘጋም ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ከትንሳኤው ፡ ኋላ ፡ አርባ ፡ ቀናት ፡ ኖሮ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ መሰረት ፡ አኑሮ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ሰው ፡ ሆኖ ፡ የመጣው ፡ ጌታ ፡ ሆኖ ፡ ሄዷል ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በውርደት ፡ የመጣው ፡ በክብር ፡ አርጓል ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አለልን ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና እያማለደልን ፡ ቤት ፡ እየሰራልን ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ያኔ ፡ መጀመሪያ ፡ በግ ፡ ሆኖ ፡ የመጣው ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ዳግም ፡ ሲመለስ ፡ ግን ፡ የጌታዎች ፡ ጌታ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በመለከት ፡ ድምፅ ፡ በመላእክት ፡ አጀብ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አብረን ፡ እንድንገባ ፡ ቶሎ ፡ እንመዝገብ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ስለስሙ ፡ ብለው ፡ የተገፉ ፡ ሁሉ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ኢየሱስ ፡ ሲከብር ፡ አብረው ፡ ይከብራሉ አዝ፦ ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x) ተወዳዳሪ ፡ የለውምና አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x) ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ በሕይወቱ ፡ እያለ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ካልካደ ፡ በስተቀር ፡ ያላየ ፡ ማን ፡ አለ? ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ክህደትን ፡ አመፅን ፡ ከምድር ፡ ሲያጠፋ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ድንበሯ ፡ ሲሰፋ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በኢየሱስ ፡ ስም ፡ ስልጣን ፡ ወንጌሉ ፡ ሲሰበክ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ምላስ ፡ ሲመሰክር ፡ ጉልበት ፡ ሲንበረከክ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ታዲያ ፡ ለምንድነው ፡ ወገኔ ፡ የምትደክም? ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ሕያው ፡ አምላክ ፡ እንጂ ፡ ግኡዝ ፡ አታመልክም ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና በዚህ ፡ አጭር ፡ ዘመኔ ፡ ኧረ ፡ ስንት ፡ አሳየኝ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ለኢየሱስ ፡ ጌትነት ፡ እኔም ፡ ምስክር ፡ ነኝ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አንቺም ፡ ምስክር ፡ ነሽ ፡ አንተም ፡ ምስክር ፡ ነህ ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና ሁላችንም ፡ እንበለው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና አዝ፦ ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x) ተወዳዳሪ ፡ የለውምና አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)