Loading
Singer
ቀማኛ ፡ ረብሸኛ ፡ ሌባ ፡ ተንኮለኛ ጨካኝ ፡ ነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ እብሪተኛ ፡ ኃይለኛ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጋር ፡ ኢኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሲደርስ ልቡ ፡ ይማረካል ፡ ይረታል ፡ በኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ሌባውን ፡ ታማኝ ፡ ያደርጋል ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ረብሸኛን ፡ ሰላማዊ ፡ ያደርጋል አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል ብዙ ፡ ተመሬያለሁ ፡ የሚለኝ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ዓለም ፡ ምን ፡ እንደሆን ፡ እኔ ፡ አውቃለሁኝ ፡ ባይ የጥበብን ፡ መሰረት ፡ ጌታን ፡ ያገኝና አምላኩን ፡ ይፈራል ፡ ዕውቀቱን ፡ ይረዳና ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ትዕቢተኛን ፡ ትሁት ፡ ያደርጋል (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ይማርካል ተስፋ ፡ የቆረጠው ፡ በሰው ፡ የተናቀው ታናሽ ፡ የተባለው ፡ ዕውቀትም ፡ የሌለው የዕውቀትን ፡ ሚስጥር ፡ ኢየሱስን ፡ አግኝቶ ሩቁን ፡ ማየት ፡ ችላል ፡ ማስተዋል ፡ ተሞልቶ ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል የተናቀውን ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል የተናቀውን ፡ ያስከብራል አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል የጐደለኝ ፡ የለም ፡ ሰላማዊ ፡ ሰው ፡ ነኝ ተኛለሁ ፡ እረፍት ፡ አለኝ ፡ ደህና ፡ አለኝ ፡ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ሲል ፡ የኖረው ፡ ሀብታም ፡ ሲያደርግ ፡ እራሱን ፡ ደግ ተረዳው ፡ በኢየሱስ ፡ መሆኑን ፡ የጠፋ ፡ በግ ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ወደ ፡ ቤትም ፡ ያስገባል (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል ሸባው ፡ በአልጋ ፡ ወድቆ ፡ በበሽታ ፡ ማቆ ቆሞ ፡ መሄድ ፡ ችሏል ፡ ኢየሱስን ፡ አውቆ የሞተው ፡ ተንስቷል ፡ የእውሩም ፡ ዓይን ፡ በርቷል እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ሽባውንም ፡ ያራምዳል ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል የሞተውን ፡ ያስነሳል አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል (፪x)