Loading
Singer
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ደስ ፡ ያሰኘህ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ደስ ፡ ያሰኘህ አድነኸኛል ፡ ከሞት ፡ መጥተህ ፡ ወዳላሁበት ከዚህ ፡ የተነሳ ፡ አረፍኩኝ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋንና ፡ አመጣሁኝ ፡ ምሥጋና ፡ ለማዳንህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና ፡ ለማዳንህ ፡ ምሥጋና ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ ተጨንቀኽልኝ ፡ ስለኔ ፡ ሰላምን ፡ ሰጠኸኝ ፡ ለኔ እንደ ፡ ወንዝ ፡ በልቤ ፡ ፈሳል ይኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ተቀበል ፡ ምሥጋና ፡ ለሰላምህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና ፡ ለሰላምህ ፡ ምሥጋና ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ በልቅሶ ፡ በሃዘን ፡ ፈንታ አስታጥቀኸኛል ፡ ደስታ መከራን ፡ በአንተ ፡ ረስቼ ፡ ይኸው ፡ ምጋናህን ፡ አብዘቼ ፡ ምሥጋና ፡ ለደስታህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና ፡ ለደስታህ ፡ ምሥጋና ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ ምንም ፡ አያሻኝ ፡ ረክቼ ጌታን ፡ አንተን ፡ ተጠግቼ ጌታ ፡ በልቤ ፡ ከብረሃል አፌም ፡ ምግናህን ፡ ያወራል ፡ በዚህች ፡ ዕውቀት ፡ እንዲህ ፡ ካረካኸኝ ፡ ብዙ ፡ ባውቅህ ፡ ምን ፡ እሆናለሁኝ ፡ ናፍቃለሁ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ ላውቅህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ስግደት ፡ ላመጣልህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ውርስ ፡ የምፈልገው ፡ ብር ፡ ወርቅን ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ያለኸን ፡ አንተ ፡ ምሻውም ፡ አንተን ፡ ነው ፡ ነገም ፡ ከዛ ፡ ወዲያ ፡ መሻቴ ፡ አንተን ፡ ነው