Loading
Singer
Updated 6d ago
ያ ፡ የጥንቱ ፡ ፍቅራችን ፡ መሃላችን ፡ የታለ ኀጢአታችን ፡ በዝቶ ፡ ጥላቻን ፡ አበቀለ ከአንተ ፡ ያልተቀበልነው ፡ ያልሰጠኸን ፡ ምን ፡ አለ ሁሉም ፡ ተረስቶ ፡ ዛሬ ፡ ትዕቢታችን ፡ ከፍ ፡ አለ አዝ:- ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x) ኀጢአት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ አይሆንም ፡ ልማት ሞትን ፡ ይወልዳል ፡ ለሕይወት ፡ ጥፋት ደሙ ፡ ያላጠበው ፡ ያልተመለሰ እናስብ ፡ እንጂ ፡ ከየት ፡ ደረሰ ምክንያት ፡ አንደርድር ፡ ለድካማችን ከሞት ፡ ያድናል ፡ መመለሳችን ኑሯችን ፡ ከንቱ ፡ ከእውነት ፡ የሚጣረስ ንሰሃ ፡ እንግባ ፡ ሳናለባብስ ቦታ ፡ አጥቶ ፡ ቅድስና ፡ ኀጢአት ፡ ተሞልቷል ፡ ቤቱ ሁሉም ፡ አንተን ፡ አልፈራም ፡ ይስታል ፡ በአንደበቱ የጥበብ ፡ መጀመሪያው ፡ አንተን ፡ መፍራቱ ፡ ጠፍቶ ሁሉ ፡ እንዳሻው ፡ ይሄዳል ፡ ቤቱ ፡ በአመጽ ፡ ተሞልቶ አዝ:- ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x) ከየት ፡ ተማርነው ፡ ወንድምን ፡ መጥላት ከነብያት ፡ ነው ፡ ወይንስ ፡ ከሓዋርያት የቀደሙትን ፡ የምናውቃቸው ፡ በመልካም ፡ ፍቅር ፡ በጸሎታቸው ለእውነት ፡ እንኑር ፡ ከቶ ፡ አንገበዝ ደሙ ፡ ያነጻናል ፡ ቶሎ ፡ እንመለስ የሰማይ ፡ ጥበብ ፡ የላይኛይቱን ከአምላክ ፡ እንለምን ፡ ይሰማል ፡ ሁሉን (፪x)