Loading
Singer
አይታለፍም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ተውቦ ፡ ሰመረ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ሁሉን ፡ ልጸራው ፡ ችለሃል ተራራውንም ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ አርገሃል (ኢየሱስ) ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ (ኢየሱስ) ፡ ትርጉም ፡ ማንነቴ (ኢየሱስ) ፡ በቀኝህ ፡ ያኖርከኝ (ኢየሱስ) ፡ የልቤ ፡ ኩራቴ (ኢየሱስ) ፡ ምሥጋናዬ ፡ አንተ ፡ ነህ (ኢየሱስ) ፡ አንተን ፡ እጠራለሁ (ኢየሱስ) ፡ ስምህ ፡ ሲያለመልም (ኢየሱስ) ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው አምላክ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ የማያልፍ ፡ የለም ምርኩዜ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለህ ትላንት ፡ ያደረከው ፡ እምነት ፡ ሆኖኛል የማይጥል ፡ እጅህ ፡ እጄን ፡ ይዞኛል አልተረታሁም ፡ እኔስ ፡ በስምህ ፡ ተወረርጄ ፊቴ ፡ አላፈረም ፡ መልሴ ፡ ፈጠነ ፡ ገባልኝ ፡ ከእጄ የማይቻለው ፡ በአንተ ፡ ተችሎ ፡ አይቼዋለሁ ለስምህ ፡ ክብር ፡ ለጌትነትህ ፡ እዘምራለሁ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ (፬x) እረኛዬ ፡ ነህ ፡ ከአንበሳው ፡ ከድብ ፡ አድነኸኛል አበቃ ፡ ሲባል ፡ የሁሉንም ፡ ቁልፍ ፡ ይዘህ ፡ ደርሰሃል ታዲያ ፡ ብዘምር ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፡ መች ፡ ይበዛና ታሪኬ ፡ ሆነህ ፡ አዳፋ ፡ ልብሴን ፡ ጥለሃልና አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ (፬x)