Loading
Singer
ኑሮ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ ታክቶኝ ፡ ኀጢአቴ ፡ አስመርሮኝ ወደ ፡ ኢየሱሴ ፡ ብመለስ ፡ የእርሱ ፡ ደግነት ፡ ማርኮኝ በድል ፡ ጐዳና ፡ ብገባ ፡ ፍቅሩ ፡ ነፍሴን ፡ ብትፈታ ጉልበቴን ፡ ለጠላት ፡ ላልሰጥ ፡ ቃል ፡ ገባሁኝ ፡ ለጌታ በመከራና ፡ በጭንቀትም ፡ ሁሉ ፡ ጌታን ፡ አመልከዋለሁ ኑሮ ፡ ያለእርሱ ፡ ጉዳት ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ግን ፡ ደስታ የመልካም ፡ ሁሉ ፡ መሰረት ፡ ይመስገን ፡ የእኛ ፡ ጌታ ስንጨነቅ ፡ የሚራራ ፡ ስንደክም ፡ ደጋፊያችን በበረሃ ፡ ዓለም ፡ እያለን ፡ ስንጠማ ፡ እርካታችን ዞሮ ፡ መግቢያችን ፡ ኢየሱስ ፡ ማረፊያችን ፡ አንተ ፡ ነህ ብንከዳህ ፡ አያዋጣንም ፡ የድሃ ፡ ጐጇችን ፡ ነህ ጌታ ፡ ጌታችን ፡ ጌታችን ፡ አስታውሰን (፪x) ብለን ፡ ተጣርተን ፡ ሳናፍር ፡ እስካሁን ፡ ተጉዘናል በነገር ፡ ሁሉ ፡ መጽናትን ፡ ከጌታ ፡ ተምረናል የሚያሳፍር ፡ ስም ፡ አይደለም ፡ የሰጠኸን ፡ ጌታችን ክርስቲያን ፡ ጀግንነት ፡ እንደው ፡ ይረዳልን ፡ ልባችን ክፉውን ፡ ሁሉ ፡ ተቃውመን ፡ ከኀጢአት ፡ ጋራ ፡ ታግለን ጉዟችን ፡ በድል ፡ ያከትማል ፡ የጌታን ፡ መስቀል ፡ ይዘን ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌ ፡ ሉያ (፪x) የነፍሳት ፡ ሁሉ ፡ ምሥጋና ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው በቸርነትህ ፡ ተገርሟል ፡ በልጅህ ፡ የዋጀኸው (፪x)