Loading
Singer
ብዙ ፡ ማስጨነቅ ፡ በብዙ ፡ ማሸበር ዙሪያዬን ፡ ሲዞሩ (፫x) በአንድ ፡ መንገድ ፡ መጥቶ ፡ በታናቸው አየሁ ፡ በሰባት ፡ መንገድ (፫x) እጆቼኔም ፡ አልሰጥም ፡ ወጀቡን ፡ አይቼው ማዕበሉን ፡ ፈርቼው (፪x) ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ ካለው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ይበልጣል ፡ አምናለሁ (፫x) ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ በጅግናው ፡ ጌታ ፎክሮበታል ፡ እንደማይረታ ሁሉም ፡ ቢናገር ፡ የስንፍና ፡ ቃል ጐልያድ ፡ እንደድምቅ ፡ የማይቀር ፡ ነው ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ በጅግናው ፡ ጌታ ፎክሮበታል ፡ እንደማይረታ ሁልም ፡ ቢናገር ፡ የስንፍና ፡ ቃል ዮርዳኖስ ፡ እንደሚከፈል ፡ የማይቀር ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መመኪያ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት ኢየሱስ ፡ ከጠላት ፡ ወጥመድ (፪x) ፈርዖን ፡ ለምን ፡ ነው መቸኮሉ ፡ ኃይሉን ፡ መጨረሱ (፫x) በእግዚአብሔር ፡ ህዝብ ፡ ላይ በትዕቢት ፡ ተነስቶ ፡ አንዲህ ፡ መገስገሱ ለፍቶ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም የሕዝቡ ፡ ጠባቂ ፡ የህዝቡ ፡ መከታ ባህር ፡ ተከፈለ ፡ ሕዝቡም ፡ ተሻገረ ፈርዖን ፡ ቀረ ፡ እዚያ የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ኣምላክ ፡ ነው ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ ስንቴ ፡ አምልጫለሁ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ መቆም ፡ አይችልም የሚጠብቅኝ ፡ የሚተኛ ፡ አይደለም ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መመኪያ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት ኢየሱስ ፡ ከጠላት ፡ ወጥመድ (፪x) ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ ከላላ ኢየሱስ ፡ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት ሆንከኝ ፡ ለእኔ ፡ አባት ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ለራሱ ፡ የለየኝ ፡ ለክብሩ ፡ የቀባኝ ተስፋ ፡ አስጨብጦኛል ፡ በመንገዴ ፡ ላይ ፡ ገብቶ ለአፍታ ፡ አንደማይተወኝ ድምጹን ፡ እየሰማሁ ፡ እከተለዋለሁ ፡ ከኋላው ፡ አሮጣለሁ ወደ ፡ ታየለኝ ፡ ግብ ፡ አልቀርም ፡ እደርሳለሁ ፡ ዘልቄ ፡ እገባለሁ ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው መቼ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ቃሉ ፡ ሊሽረው ወጥመዴን ፡ ስብሮ ፡ ያሻግረኛል የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ ያወርሰኛል