Loading
Singer
ቀኑ ፡ እንዴት ፡ ይገፋል ፡ ያለመጨነቅ በሃሳብ ፡ ማጥ ፡ ውስጥ ፡ መማቀቅ (፪x) ሳይሞላለት ፡ ዛሬን ፡ ነገን ፡ ሲፍጨረጨር በሥጋት ፡ ብዛት ፡ ሲወጠር (፪x) የሰው ፡ ሕይወት ፡ በምድር ፡ ሰልፉ ፡ እንዴት ፡ ብርቱ ፡ ነው ማነው ፡ ከዚህ ፡ መዓት ፡ የሚገላግለው አዝ:- የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ ያለው መፍትሄው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ኢየሱስ (፲፪x) የሁሉን ፡ ሚስጥር ፡ ቁልፉን ፡ ይዘሃል በአሰራርህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል በሰማይ ፡ በምድር ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው እንዲህ ፡ አታድርግ ፡ የሚልህ ፡ ማነው ሕይወትም ፡ በድንገት ፡ ሲለብስ ፡ ደመና ደጅ ፡ ሲወጣ ፡ ገበና (፪x) ያላሰቡት ፡ ሲደርስ ፡ ያሰቡት ፡ ሳይሞላ ሰው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሲጣላ (፪x) የሰው ፡ ሕይወት ፡ በምድር ፡ ሰልፉ ፡ እንዴት ፡ ብርቱ ፡ ነው ማነው ፡ ከዚህ ፡ መዓት ፡ የሚገላግለው አዝ:- የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ ያለው መፍትሄው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ኢየሱስ (፲፪x) የሁሉን ፡ ሚስጥር ፡ ቁልፉን ፡ ይዘሃል በአሰራርህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል በሰማይ ፡ በምድር ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው እንዲህ ፡ አታድርግ ፡ የሚልህ ፡ ማነው