Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ ወደ ፡ እኔ ፡ ጩህ ፡ እኔም ፡ እመልሳለሁ ታላቁንም ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ አሳይሃለሁ በቃልህ ፡ ስላልከኝ ፡ እንዲህ ፡ እጮሃለሁ እንድትፈውሰኝ ፡ ሥምህን ፡ ጠራለሁ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ በድካም ፡ ማዕበል ፡ ሕይወቴ ፡ ተገፍቶ በሚሰብር ፡ በትር ፡ ክፉኛ ፡ ተመቶ የታመቀው ፡ ስቃይ ፡ ልብን ፡ እየጣሰ እንባን ፡ አስክትሎ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ደረሰ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ አልጥልህም ፡ ብለህ ፡ ከቶም ፡ አለቅህም የገባህልኝ ፡ ቃል ፡ አልተዘነጋኝም እኔ ፡ ፈዋሽህ ፡ ነኝ ፡ ብለህ ፡ የፈወስከኝ ከጉስቁልናዬ ፡ ና ፡ ዛሬም ፡ አድነኝ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ የፈረሰውን ፡ አዳሽ ፈዋሼ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእንባዬ ፡ አባሽ ሰዎች ፡ ያላዩትን ፡ ቁስሌን ፡ ያየህልኝ አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህልኝ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ