Loading
Singer
ልቤ ፡ አንተን ፡ ይላል መንፈሴም ፡ ወዳንተ ፡ ይገሰግሳል ጉጉቴ ፡ አንተን ፡ ማክበር ፡ ነው ፍላጎቴ ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው የእኔ ፡ ደስታ ፡ አንተን ፡ ማስደሰት ፡ ነው ዓላማዬ ፡ የአንተ ፡ ዓላማ ፡ ነው የእኔ ፡ ደስታ ፡ ደስ ፡ ሲልህ ፡ ማየት ፡ ነው ዓላማዬ ፡ የአንተ ፡ ዓላማ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x) ከምትወደው ፡ ጋራ ፡ እስማምለሁ የምትጠላው ፡ ለኔ ፡ ጠላቴ ፡ ነው በመታዘዝ ፡ ፍቅሬን ፡ እገልጻለሁ ዝቅ ፡ ማለቴ ፡ አንተን ፡ ከፍ ፡ ላደርግ ፡ ነው መኖር ፡ ትርጉም ፡ ሚስጥሩ ፡ አንተ ፡ ነህ እወዳለሁ ፡ ዛሬም ፡ ልገዛልህ (፪x) ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደሚናፍቅ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች (፪x) ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደልብህ ፡ ሆኜ ፡ ልኑርልህ ልቤን ፡ ትቼ ፡ ያየኸውን ፡ ልይልህ መንፈስን ፡ ከኔ ፡ አትውሰደው አጥፍ ፡ ልስገድ ፡ ሁሌም ፡ ላገልግለው ከውሃ ፡ ውስጥ ፡ እንደወጣ ፡ ዓሣ መኖር ፡ አልችልም ፡ ተለይቼ ፡ ጌታ (፪x) ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደሚናፍቅ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች (፪x) ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x)