Loading
Singer
ውለታውን ፡ ተናግሮ ፡ ያበቃ እግዚአብሔርን ፡ አክብሮ ፡ የረካ ማነው ፡ እርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ያለቀበት ያልተረዳ ፡ የዛሬውን ፡ ምህረት ከትናንቱ ፡ በላይ ፡ እንደሆነ በብዙ ፡ እጥፍ : ብዝቶ፡ እንደገነነ የዛሬውን ፡ ቸርነት/ደግነት ፡ የረሳ ለማመሥገን ፡ በፍጥነት ፡ ይነሳ (፪x) አዝ፦ እኔስ ፡ ከትናንቱ ፡ የዛሬው ፡ ባሰበኝ ካለፉት ፡ ዓመታት ፡ የሆነው ፡ ላቀብኝ ፍቅር ፡ ደግነቱ ፡ ምህረቱ ፡ ገነነ ከማስበው ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሆነ እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ሁሌ ፡ እያሳቀኝ አፌን ፡ በምስጋና: ምላሴን ፡ በዕልልታ ፡ እየሞላብኝ ነፍሴን ፡ የሚያረካ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ ዘወትር ፡ በየለቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታዬ ፡ አመሠግናለሁ (፭x) ተናግሬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ተዓምሩን ይገልጠዋል ፡ በድጋሚ: ክብሩን በላይ ፡ በላይ ፡ እየጨማመረ እያበዛ ፡ ደግሞ ፡ እያከበረ በዘመናትና ፡ በዓመታቱ ሳያጓድል ፡ ሳይሰስት ፡ ንብረቱን ያስጉዘኛል/ያስኬደኛል ፡ በድል ፡ ሰረገላ ምን ፡ ልበለው ፡ ከተመሥገነ ፡ ሌላ (፪x) ምስጋናዬ የበዛበት ምክንያቴ ብዙ ብዙ ነው የተጙዝኩበት ጎዳና ያ ዘመን ምስክሬ ነው ካንደኛው የህይወት ምዕራፍ ወደሌላው ስሸጋገር ብርሀኑን እያበራ የመራኝ አምላኬ ይክበር (፪x) ማዳኑን ፡ ስላየሁ ፡ አመሠግናለሁ (፫x) ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፫x) ቀኖቹ ፡ ቢያወሩ ፡ ቢመሰክሩት (፫x) አቤት ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራት (፫x) ሥሙን ፡ እባርከዋለሁ (፫x) ሥሙን ፡ እቀድሰዋለሁ (፫x) ነፍሴና ፡ ሥጋዬ ፡ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አቅርቡ አጥንቶቼም ፡ ጭምር ፡ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አቅርቡ የሰራላችሁን ፡ የማዳኑ ፡ ሥራ ፡ አስቡ (፪x) አልበቃኝም ፡ አመሥግኜው (፪x) ፡ አልበቃኝም እኔ ፡ አልረካሁም ፡ አመሥግኜው (፪x) ፡ አልረካሁም (፪x)