Loading
Singer
እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ ብዙ ፡ ዓመት ፡ አለፈ ፡ ጌታ ፡ እየረዳኝ ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ድንቁ ፡ በህይወቴ ለእኔስ ፡ ተለየብኝ ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምኮራበት ለክፉ ፡ ቀኔም ፡ ምደገፍበት ወረት ፡ አያውቀው ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፍቅሩ ፡ እውነተኛ ፡ የልብ ፡ የሚያደርስ እዚህ ፡ እደርሳሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም የሚሆን ፡ አይደለም ጌታ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ እንዲህ ፡ እሆናለሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም የሚሆን ፡ አይደለም ጌታ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ ይገርማል (፪x) ፡ አሰራሩ ፡ ይገርማል ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል ይደንቃል (፪x) ፡ ያረገልኝ ፡ ይደንቃል ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል አይገርማችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች ፡ በሙሉ ጌታ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ ፡ ለምስኪኑ እርሱ ፡ በእኔ ፡ ሊከብር ፡ መስዋቴን ፡ ወዶታል በደረቁ ፡ አጥንቴ ፡ ዝማሬን ፡ ጨምሮአል ይገርማል (፪x) ፡ አሰራሩ ፡ ይገርማል ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል ይደንቃል (፪x) ፡ ያረገልኝ ፡ ይደንቃል ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ ብዙ ፡ አመት ፡ አለፈ ፡ ጌታ ፡ እየረዳኝ ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ድንቁ ፡ በሕይወቴ ለእኔስ ፡ ተለየብኝ ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምኮራበት ለክፉ ፡ ቀኔም ፡ ምደገፍበት ወረት ፡ አያውቀው ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፍቅሩ ፡ እውነተኛ ፡ የልብ ፡ የሚያደርስ