Loading
Singer
ቀን ፡ ጠብቆ ፡ ገሸሽ፡ ይልብኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ? አለልኝ ፡ ስል ፡ ዓይንሽ/ህ ፡ ለአፈር ፡ ይለኛል ፡ ወይ? ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም (፪x) እርሱማ ፡ እየበደልኩት ፡ ቻለኝ እርሱማ ፡ እየራቅኩት ፡ ቀረበኝ እርሱማ ፡ ሰለቸኝ ፡ ወዲያ ፡ አላለኝ (፪x) ብሸሸው ፡ ብርቀው ፡ አለቅ ፡ ያደረገኝ ጌታ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! ከ'ነማንነቴ ፡ የወደደኝ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! (፪x) እያባበለኝ (፫x) ተሸከመኝ (፫x) በምክሩም ፡ ሲያስተምረኝ ፡ ደጉን ፡ ሲያሰየኝ እንደ ፡ አባት ፡ ሲቀጣኝ ፍቅር ፡ ማለት ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ አወኩኝ መልሶ ፡ ሲያባብለኝ ፡ አለው ፡ ሲለኝ ፡ ሲያበረታታኝ ፍቅር ፡ ማለት ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ አወ'ኩኝ (፪x) እያባበለኝ (፫x) ተሸከመኝ (፫x) ቀን ፡ ጠብቆ ፡ ገሸሽ ፡ ይልብኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ? አለልኝ ፡ ስል ፡ ዓይንሽ/ህ ፡ ለአፈር ፡ ይለኛል ፡ ወይ? ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም (፪x) እርሱማ ፡ እየበደልኩት ፡ ቻለኝ እርሱማ ፡ እየራቅኩት ፡ ቀረበኝ እርሱማ ፡ ሰለቸኝ ፡ ወዲያ ፡ አላለኝ (፪x) ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ነጥቆ ፡ ተስፋን ፡ የጨመረልኝ ጌታ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! የተቆረጠውን ፡ የቀጠለልኝ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! (፪x) እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ (፫x)