Loading
Singer
ከመፈጠሬ ፡ ከመታሰቤ ፡ ጀምሮ የማትለወጥ ፡ የማትቀየር ወረት ፡ የሌለበት ፡ አንተን ፡ ነው ፡ ያየሁት (፪x) አዝ፦ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ እውነተኛ ፡ አፍቃሪ (፪x) የእኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አንተ ፡ ነህ ጊዜ/ዘመን ፡ የማይለውጥህ (፪x) ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ለካስ ፡ አለው ፡ መጨረሻ ለካስ ፡ እኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ በቃ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ማሸሻ የሰው ፡ ልጅ ፡ ሆኖ ፡ የሰው እየተባለ ፡ ማነው ከሰማይ ፡ መጣ ፡ ከላይ አላስችል ፡ ብሎት ፡ ሲያይ ከሞት ፡ አወጣኝ ፡ ከሞት ደርሶልኝ ፡ ካለሁበት ተናገር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲሉኝ ለዚህ ፡ ነው ፡ ቃላት ፡ ያጠረኝ ሰማይ ፡ ይናገር ፡ ምድርም ስላንተ ፡ ላውራ ፡ ዘለዓለም (፪x) አዝ፦ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ እውነተኛ ፡ አፍቃሪ (፪x) የእኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አንተ ፡ ነህ ጊዜ/ዘመን ፡ የማይለውጥህ (፪x) ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ለካስ ፡ አለው ፡ መጨረሻ ለካስ ፡ እኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ በቃ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ማሸሻ