Loading
Singer
እውነተኛ ፡ ሰላም ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ የገባኝ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ስይዝ ፡ ጌታ ብዙ ፡ ተቅበዘበዝኩ ፡ ደህንነት ፡ ፍለጋ በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ላገኘው ፡ አንተ ፡ ጋ ምቾቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ነህ እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ልቤ ፡ ያረፈብህ (፪x) ልቤ ፡ ያረፈብህ (፬x) (ያረፈብህ (፰x)) ወርቅ ፡ ዕንቁ ፡ ቢሞላ ፡ ላይሰጠኝ ፡ ሰላም ዕውቀት ፡ ቢደረደር ፡ አያሳርፍም ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ ፡ ጥያቄዋ ፡ በዝቶ መመለስ ፡ የሚችል ፡ ከወዴት ፡ ተገኝቶ አንተ ፡ ስትገባ ፡ ወደ ፡ ሕይወቴ ተለዋወጠ ፡ ማንነቴ ጥያቄ ፡ ሁሉ ፡ ተመለሰ ሰላም ፡ ደስታ ፡ በውስጤ ፡ ፈሰሰ (፪x) በለስ ፡ ባታበቅል ፡ ፍሬዋ ፡ ባይገኝ ምድራዊ ፡ ነገሬ ፡ ቢጨላልምብኝ ቢጐድል ፡ ቢሞላ ፡ እኔ ፡ አልገረምም በዚህ ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ሰላሜ ፡ አይጐልም የማዳኑን ፡ ክንድ ፡ አልብሶኛል መጐናጸፊያን ፡ ደርቦልኛል በአምላኬ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ ለዘለዓለም ፡ በደስታ ፡ ኖራለሁ (፪x) እውነተኛ ፡ ሰላም ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ የገባኝ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ስይዝ ፡ ጌታ ብዙ ፡ ተቅበዘበዝኩ ፡ ደህንነት ፡ ፍለጋ በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ላገኘው ፡ አንተ ፡ ጋ ምቾቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ነህ እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ልቤ ፡ ያረፈብህ (፪x) ልቤ ፡ ያረፈብህ (፬x) የሚያውቁኝ ፡ በሙሉ ፡ እጅግ ፡ ተገረሙ እንዲህ ፡ የሚያሳርፍ ፡ "ምን ፡ አገኘ?" ፡ እያሉ ፍፁም ፡ መረጋጋት ፡ እርፍ ፡ ማለት የትም ፡ አይገኝም ፡ በሌለህበት ሁሉን ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼህ ተደላደልኩኝ ፡ አረፍኩብህ የማይለወጥ ፡ ፍቅርህ ፡ ሲነካኝ ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ሆነብኝ (፪x) የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ሰላም ፡ የሆነኝ ፡ ኢየሱስ ማንም ፡ ከእንግዲህ ፡ ኢየሱስ የማይለያየኝ ፡ ኢየሱስ ቁስሌን ፡ ፈውሶ ፡ ያረገኝ ፡ ደህና አከብረዋለው ፡ ክብሬ ፡ ነውና (፬x)