Loading
Singer
በማበሉ መጥመፍ ፍርሃት ሲከበን በህይወት መፍገምገም ደፋ ቀና ስንል/2 ዝማሬ ተውጦ ሲተካ ምሬት ጌታ ትደርሳለህ በወሳኝ ሰዓት/2 አንተን ለታመነህ ለተደገፈህ እውነተኛ ወዳጅ ረዳት አንተ ብቻ ነህ አንተን ለታመነው ለተደገፈህ እውነተኛ ረዳት አባት አንተ ነህ አባት አንተ ነህ/2 እውነተኛ ረዳት አባት አንተ ነህ መቅሰፍት በምድር ላይ በድንገት ሲከሰት ብዞችን ጠራርጎ ሲወስድ በቅፅፈት/2 አንተን ለታመኑህ መጠለያ አምባ ነህ ከምሬት ከለቅሶ ከሃዘን ታድናለህ/2 አንተን ለታመነህ ለተደገፈህ እውነተኛ ወዳጅ ረዳት አንተ ብቻ ነህ አንተን ለታመነው ለተደገፈህ እውነተኛ ረዳት አባት አንተ ነህ አባት አንተ ነህ/2 እውነተኛ ረዳት አባት አንተ ነህ ማምለጫ መሸሻ መንገዱ አንድ ነው እርሱም እየሱስ/2 ለሰማው ለታዘዘው ከሞት የሚያድነው እየሱስ ብቻ ነው/2