Loading
Singer
የክሱን ፡ ክምችት ፡ የዕዳውን ፡ ጽህፈት ደምስሰህልናል ፡ በመስቀልህ ፡ ምህረት አንተ ፡ አጽድቀኸናል ፡ ማነው ፡ የሚከሰን ከጸናችው ፡ እጅህ ፡ የለም ፡ የሚነጥቀን ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ ተረታሁኝ ፡ ብሎ ፡ ጠላትም ፡ ባይተኛ የማንተቀላፋ ፡ ጌታ ፡ አለህ ፡ ለእኛ ደምፅህን ፡ ሲሰማ ፡ አጥማጅህ ፡ ገለል ፡ ይላል ከመከራም ፡ ስጋት ፡ በአንተ ፡ ያመነ ፡ ያርፋል ተከልሎ ፡ ይኖራል አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ ከሳሻችን ፡ ወድቆ ፡ እኛ ፡ ተነስተናል ጉልበታችን ፡ ፀንቶ ፡ እነሆ ፡ ቆመናል ታዳጊያችን ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን ፡ እንበልህ ከአዳኙ ፡ ወጥመድ ፡ የወጣን ፡ ሕዝበህ ማርኮናል ፡ ፍቅርህ አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ