Loading
Singer
አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) የዓለምን ፡ ደስታ ፡ እናሳይሽ ፡ ቢሉኝ እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ተነስቼ ፡ ሄድኩኝ የሙዚቃው ፡ ጩኀት ፡ ጭፈራ ፡ ዘፈኑ ለዐይን ፡ የሚስበው ፡ የመብራት ፡ ድምቀቱ ቅልጥ ፡ ካለው ፡ መንደር ፡ እግሬ ፡ እንደወጣ ብፈልግ ፡ አጣሁት ፡ የነበረው ፡ ደስታ አወይ ፡ አወይ ፡ የዓለም ፡ ደስታ ብልጭ ፡ ብሎ ፡ ወዲያው ፡ የሚጠፋ ቋሚ ፡ የሆነ ፡ ደስታ ፡ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ፡ ከእርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው አወይ ፡ አወይ ፡ የዓለም ፡ ደስታ በኖ ፡ የሚያልቅ ፡ ልክ ፡ እንደጤዛ እውነተኛ ፡ የውስጥ ፡ ሰላሜ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ለእኔ አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) ክቡሩን ፡ ሰው ፡ አየሁ ፡ እራሱን ፡ ሲጥል ትንሹ ፡ ትልቁ ፡ በወይን ፡ ጠጅ ፡ ሲሰክር እርግጥ ፡ ነው ፡ ለጊዜው ፡ ደስታንም ፡ ይሰጣል ማታ ፡ ላይ ፡ አስቆ ፡ ጠዋት ፡ ያስለቅሳል እኔ ፡ ስላየሁኝ ፡ እመሰክራለሁ የደስታው ፡ ምንጭ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ሁሉም ፡ ነገር ፡ ቢተርፍ ፡ ቢበዛ እንደ ፡ ልብህ ፡ ብትሆን ፡ እንደ ፡ አሻህ የሰላሙን ፡ ንጉሥ ፡ አለቃ ካላገኘህ ፡ መቼም ፡ አትረካ እግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ፍፁም ፡ የሆነ ማይወሰድ ፡ ሰላም ፡ እያለ አትባክን ፡ አትድከም ፡ ይብቃህ እርፍ ፡ በል ፡ አይ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) አንዱ ፡ ለመደሰት ፡ ሲደክም ፡ ሲለፋ ሌላው ፡ ሰላም ፡ አጥቶ ፡ እራሱን ፡ ሲያጠፋ ዓለም ፡ ልትሰጠኝ ፡ የማትችለው ፡ ሃብቴ ከላይ ፡ ያገኘሁት ፡ ትልቁ ፡ ንብረቴ ምንም ፡ ነገር ፡ ሳይኖር ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ እርካታ አሜን ፡ ያስብለኛል ፡ እንኳን ፡ ሆንኩ ፡ የጌታ ብርና ፡ ወርቅ ፡ የማይተካው ሚበልጥ ፡ ነው ፡ እኔ/አንተ ፡ ጋር ፡ ያለው አቤት ፡ እኔ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ/ክርስትያን ፡ እድለኛ ፡ ነህ የሚያሳርፍ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ያለኝ (፪x) አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x) ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)