Loading
Singer
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ልሂድ ፡ ልያዘው ተራራማው ፡ ምድር ፡ የእኔው ፡ እኮ ፡ ነው እርጅና ፡ አያውቀኝ ፡ እድሜ ፡ አይወስነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ ጉልበታም ፡ ሰው ፡ ነኝ ልቤ ፡ አ ይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ለውጥን ፡ ያመጣል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ይመነጥራል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዪ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ እልፍ ፡ ልበል ፡ ልሂድ ፡ ልተወው የደከምኩበትን ፡ ከተመኘኸው አልሟገትም ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ ብዬ ፈቀቅ ፡ ልበል ፡ መብቴን ፡ ጥዬ በፊቴ ፡ ወጥቷል ፡ የሚዋጋልኝ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ እወጣለሁኝ የአባቶች ፡ አምላክ ፡ ላያሳፍረኝ ርሆቦት ሆኖ፡ በምድር ፡ አሰፋኝ አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ልሂድ ፡ ልያዘው ተራራማው ፡ ምድር ፡ የእኔው ፡ እኮ ፡ ነው እርጅና ፡ አያውቀኝ ፡ እድሜ ፡ አይወስነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ ጉልበታም ፡ ሰው ፡ ነኝ ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ለውጥን ፡ ያመጣል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ይመነጥራል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ (አልሰማም) እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ (እሄዳለሁ) ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ (እሄዳለሁ) እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው እርሱ ፡ አምላክ ፡ ተብሎ ፡ ይጠራ ክርክር ፡ አላውቅበትም ጊዜ ፡ አልወስድም ፡ ከእናንተ ፡ ጋራ እጮሃለሁ ፡ ዛሬ ፡ እንደጥንቱ ይሰማኛል ፡ ስለው ፡ አቤቱ መሰዊያው ፡ ላይ ፡ በእሳት ፡ ተገልጦ ይኸው ፡ ይታይ ፡ እርሱ ፡ ከፍ ፡ ብሎ (፪x) እወራረዳለሁ ፡ በአምላኬ ፡ በሰማይ ፡ ባለው እወራረዳለሁ ፡ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ታማኝ ፡ ነው እወራረዳለሁ ፡ ቀኑ ፡ አያልቅም/አያልፍም ፡ ጌታ ፡ ሳይታይ እወራረዳለሁ ፡ አማላኬ ፡ ነው ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)