Loading
Singer
(እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ) (፪x) በኃጢአቴ ፡ ሙታን ፡ በነበርኩ ፡ ጊዜ ፡ ሳላይህ ፡ ያየኸኝ ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሀይወትን ፡ ፡ ሰጠኸኝ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ልዘርጋ ፡ እንጂ አንተ ፡ የፍቅር ፡ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ የማያልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ አያረጂ ከአስፈሪው ፡ ነበልባል ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ከገሃነም ፡ ዳንኩኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ እኔም ፡ እንደ ፡ ጻድቃን ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ጸድቀሃል ፡ ተባልኩኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ በኃጢያቴ ፡ ምክንያት ፡ የሞትኩኝ ፡ ነበርኩኝ እኔም ፡ በእግዚአብሔር ፡ በአምላኬ ፡ ታሰብኩኝ የመርገም ፡ ጨርቄን ፡ ከላዬ ፡ ገፈፈው ጽድቅን ፡ አለበሰኝ ፡ (የሚከሰኝ ፡ ማን ፡ ነው) (፪x) አዝ እወድሃለሁ ፡ ጌታ እግዚአብሔርም ፡ ከወደደን ፡ ከትልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ ፡ በኃጢአታችንና ፡ በበደላችን ፡ ሙታን ፡ በነበርን ፡ ጊዜ ከክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ሰጠን ፡ ሰው ፡ ዞር ፡ ብሎ ፡ አያየኝ ፡ ቢሆንማ ፡ ኑሮ ፡ ምህረት ፡ በሰው ፡ እጅ እንኳን ፡ ለጽድቅ ፡ ልሆን ፡ እንኳን ፡ ለሌላው ፡ ሰው ፡ ለራሴም ፡ አልበጅ ዓይኑ ፡ እንዳየች ፡ ሳይሆን ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማች ፡ ሳይፈርድ ፡ አጸደቀኝ ኧረ ፡ ይገርማል ፡ ኧረ ፡ ይገርማል ፡ ሰዎች ፡ እኔንም ፡ አዳነኝ የማይገባኝን ፡ እወድሃለሁ ፡ጌታ ፡ የሕይወትን ፡ አክሊል ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ በነጻ ፡ ሰጠኸኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ስምህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ እውድሃለሁ ፡ የሱስ አዝ (እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ) (፪x)