Loading
በባዶነቴ ፡ አግኝተኀኛል አንተ ፡ እኔን ፡ መውደድ ፡ ያስገርመኛል አወዳደድህ ፡ ከመውደድ ፡ ያልፋል ወደድኩህ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያስገርማል ለምንድን ፡ ነው ፡ አልልህም ስራህ ፡ ጠፍቶኝ ፡ አልጠይቅህም የምልህ ፡ ግን ፡ አንድና ፡ ግልጽ ፡ ነው ስለወደድከኝ ፡ ወድጄሃለሁ አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ እወድሃለሁ (፪x) ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (፪x) ወድጄሃለሁ ወድጄሃለሁ ለመውደዴ ፡ ገደብ ፡ የለኝም ምገልጸበት ፡ ቋንቋም ፡ አላገኝም ብቻ ፡ ነፍሴ ፡ አፍቅራሃለች እንደወደድካት ፡ ትወድሃለች አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ እወድሃለሁ (፪x) ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (፪x) የአንተ ፡ ፍቅር ፡ መውደድህ ፡ አያልቅም መውደዴ ፡ ግን ፡ የአንተን ፡ ፍፁም ፡ አይገልጸውም አይገልጸውም ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ በትንሿ ፡ ልቤ ፡ አቅሜ ፡ ቢሆንም ፡ ይሄው ፡ እወድሃለሁ አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ እወድሃለሁ (፪x) ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (፪x) እወድሃለሁ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.