Loading
Singer
ኢትዮጵያ ፡ ሃገሬ ፡ ኢትዮጵያ መልካም ፡ እንዲሆንልሽ ፡ ዛሬ ስሚልኝ ፡ ይህቺን ፡ ዝማሬ (፪x) አምላክሽ ፡ እኮ ፡ ቀናተኛ ፡ ነው ለሌላ ፡ አማልክት ፡ መስገድሽ ፡ ምነው ለሱ ፡ ለአምላክሽ ፡ ብቻ ፡ ስገጂ እጆችሽንም ፡ ወደእርሱ ፡ ዘርጊ አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x) ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x) እርሱ ፡ እኮ ፡ ላንቺ ፡ መፍትሔ ፡ አለው የሚጠራሽ ፡ ሊያሳርፍሽ ፡ ነው ነይ ፡ ወደሱ ፡ ሸክምሽ ፡ ከብዷል ተጠጊው ፡ እርሱን ፡ ያሳርፍሻል አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x) ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x) ሊገነባሽ ፡ ነው ፡ በአዲስ ፡ ድንጋይ ተነስቷል ፡ ባንቺ ፡ ኤልሻዳይ አንቺም ፡ ተነሺ ፡ ተቀበይው አምላኬ ፡ እንተ ፡ ውዴ ፡ ነህ ፡ በይው አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x) ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x) ኢትዮጵያ ፡ ፈጥና ፡ እጆቿን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትዘረጋለች ፡ (አሜን) ኢትዮጵያ ፡ ሃገሬ ፡ ኢትዮጵያ መልካም ፡ እንዲሆንልሽ ፡ ዛሬ ስሚልኝ ፡ ይህቺን ፡ ዝማሬ (፪x)