Loading
Singer
ራቅም አልልም ማንንም ፍለጋ እጠብቅሃለሁ እኔም እስኪነጋ/2 እንዳንተ አምላኬ ማንም አይሆነኝም እጠብቅሃለሁ አንተ ብትዘገይም/2 ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2 ዝም ብትለኝም አውላላ ሜዳ ላይ ለበጎ ይሆናል አላማህ በኔ ላይ ምንም ቢደርስብኝ አላማርርህም እምነቴ ሊፈተን ችግርን ያየህልኝ ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2 እግዚአብሔር ሰጠን እግዚአብሔር ወሰደው አላጉረመርምም ፃድቅ ነው በስራው አምላኬ ትልቅ ነው ስንፍና አላወራም ስርዓቱን እንድማር ቢያስጨንቀኝም ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2 እንደተናገረው ቃል እንደገባልኝ አደርጋለሁ ብሎ ተስፋ እንደሰጠኝ እንዲሁ እንዳለው እንደሚያደርግልኝ አልጠራጠርም ጌታን አምናለሁኝ አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2